እንግሊዝ በታንዛኒያ የሰው አልባ አውሮፕላን አገልግሎት ላይ ልታውል ነው

ከደም ባንክ ወደ ክሊኒኮች የሚደረገውን የደም አቅርቦት በአፍሪካ ሃገራት ቀልጣፋ ለማድረግ የሚረዳ የሰው አልባ አውሮፕላን አገልግሎት ተግባራዊ እንደምታደርግ እንግሊዝ ገልጸች፡፡ የዚህ አገልግሎትና ድጋፍ ዋናው ዓላማም ለደም አቅርቦት የሚፈጀውን ሰዓት በከፍተኛ ሁኔታ ማሻሻል መሆኑ ነው የተነገረው፡፡ በታንዛኒያ ተግባራዊ የሚደረገው ዚፕ ላይን (Zipline's drones) በመባል የሚጠራው ይህ የሰው አልባ አውሮፕላን የጂ.ፒ.ኤስ አቅጣጫን በመጠቀም የሚሰራ መሆኑም ተነግሯል፡፡ በንድፈ ሃሳብ ደረጃም ድሮኖቹ እስከ 290 ኪሎ ሜትር መጓዝ የሚችሉ እንደሆኑና ከመሬትም 152 ሜትር ከፍታ ላይ እንደሚበሩ ነው የተነገረው፡፡ ታንዛኒያ ፣ ሩዋንዳና ማላዊም ድሮኖቹን እንደሚጠቀሙ ተነግሯል፡፡ በፈረንጆቹ 2017 አገልግሎቱን የሚጀምረው ሰው አልባ አውሮፕላን በወሊድ ጊዜ ለእናቶች የሚያስፈልገውን የደም አቅርቦት በፍጥነት ተደራሽ ለማድረግ እንደሆነና ከዚህ ቀደም ይፈጅ የነበረውን 110 ደቂቃ ወደ 19 ደቂቃ ዝቅ ያደርገዋል ተብሏል፡፡

http://www.bbc.com/news/technology-38450664