የአውሮፓ ህግ አውጪዎች የደህንነት ምርቶች የውጭ ንግድ ላይ ቁጥጥር ለማድረግ ተስማሙ

የህብረቱ አባል ሃገራት የተለያዩ አካላት ቴክኖሎጂዎቹን በመግዛት ለህገ-ወጥ ተግባር እያዋሉት ነው በሚል ለስለላ ተግባር የሚውሉ መሳሪያዎች ላይ የውጭ ንግድ ቁጥጥር ማሻሻያ ለማድረግ መስማማታቸው ተነግሯል፡፡ በህብረቱ  ቁጥጥር ለማድረግ ከተስማሙበት መካከልም የሞባይል ስልክ ጥሪዎች ለመጥለፍ የሚውሉ መሣሪያዎች፣ የኮምፒውተር መበርበሪያ መሳሪያዎች እና የይለፍ-ቃል መስበሪያዎች ይገኙበታል፡፡ የህብረቱ የንግድ ኮሚቴም በ34 ድምጽ የኤክስፖርት ቁጥጥሩ ላይ ማሻሻያ ለማድረግ ተስማምተዋል፡፡ የአውሮፓ ህግ አውጪዎችም የአጥፊ ሶፍትዌሮች (malware)፣ ለስለላ ተግባር የተፈበረኩ ሶፍትዌሮች (spyware) እንዲሁም በቴሌኮም አማካኝነት የኢንተርኔት መሰለያ ቴክኖሎጂዎች በሰብኣዊ መብት እና የደህንነት ስጋት ማደጉ እንዳሳሰበው ገልጿል፡፡ ተቋሙም የቁጥጥር ስርዓቱን በማዘመን የውጭ ንግድ ላይ ማሻሻያ ለማድረግ መወሰኑን አሳውቋል፡፡

https://www.reuters.com/article/us-eu-trade-torture/eu-lawmakers-back-exports-control-on-spying-technology-idUSKBN1DN1R6