የMTN ግሩፕ በኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ገለጸ

የደቡብ አፍሪካው የMTN ግሩፕ (Mobile Telephone Networks) ኢትዮ-ቴሌኮም ከግሉ ዘርፍ ጋር በሸር እንዲሰራ መንግስት መወሰኑ ትልቅ እርምጃ መሆኑን አስታወቀ፡፡ ሮይተርስ እንደዘገበው የMTN ግሩፕ በሁኔታው መደሰቱንና በቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፍ አህጉሪቱን በአንድ እርምጃ ወደፊት ለማስፈንጠር የተያዘውን አጀንዳ ከፍ እንደሚያደርገው አስታውቋል፡፡ MTN አክሎ እንደገለጸው ሂደቱ ከኢትዮ-ቴሌኮም ጋር በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳለውና ይህም የሁለቱንም አካላት ተጠቃሚነት የበለጠ እንደሚያረጋግጥ ለሮይተርስ ተናግሯል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ሰሞኑን በወሰነው መሰረት የኢትዮጵያን አየር መንገድ ጨምሮ ኢትዮ-ቴሌኮምና ሌሎች ኩባንያዎች ለውጭና ለውስጥ የግል ባለሃብቶች በሸር ለመስራት መወሰኑን ዘገባው አስታውሷል፡፡

https://www.reuters.com/article/ethiopia-privatisation-mtn-group/mtn-says-ethiopias-telecoms-market-a-natural-fit-for-south-african-firm-idUSL5N1T82JF