ብሔራዊ የስፓሻል ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ፖሊሲ ጸደቀ

በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) የተዘጋጀው ብሔራዊ የስፓሻል ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ፖሊሲ ጥቅምት 4 ቀን 2009 ዓ.ም ጸደቀ፡፡

የሚኒስትሮች ም/ቤት ጥቅምት 4 ቀን 2009 ዓ.ም ባካሄደው 16ኛ መደበኛ ስብሰባ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) ተዘጋጅቶ በቀረበው ብሔራዊ የስፓሻል ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ከተወያየ በኋላ ማሻሻያዎችን በማከል ፖሊሲው በስራ ላይ እንዲውል ም/ቤቱ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

የፖሊሲው ዋነኛ ዓላማ የስፓሻል ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ባለቤትነትን በማረጋገጥና በመጠቀም ጥራቱን የጠበቀ ወቅታዊና አስተማማኝ ስፓሻል ኢንፎርሜሽን ለሁሉም ተጠቃሚዎች በማቅረብ የሀገሪቱን የልማት ግቦች ለማሳካት ድጋፍ ማድረግ ሲሆን፤ ከዚህም በተጨማሪ በስፓሻል ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ አማካኝነት የሚፈጠሩ ስጋቶችን በመቀነስ የሀገር ደህንነትን ማስጠበቅ የፖሊሲው ሌላው ዓላማ ነው፡፡