የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በእስራትና በገንዘብ ተቀጣ

አቶ አብደላ አብድራህማን የሱፍ የተባለው ግለሰብ በፈጸመው የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ የፌዴራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 4ኛ የወንጀል ችሎት ተከሳሹ በ9 አመት ጽኑ እስራትና በ75ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፎበታል፡፡ግለሰቡ ይጠቀምባቸው በነበሩት ሕገ-ወጥ የቴሌኮም ማጭበርበሪያ መሳሪያዎች አማካኝነት የውጭ ሀገር የስልክ ጥሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ የስልክ ጥሪዎች በመቀየር ወንጀሉን የፈጸመ ሲሆን፤ በዚህም ከጥር 3/2006 እስከ ጥቅምት 15/2007 ዓ.ም ድረስ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ጥሪዎች ወደ ኢትዮጵያ የተደወሉ 1 ሚሊዮን 307ሺ 23 ደቂቃ ርዝማኔ ያላቸውን ጥሪዎች በማጭበርበር (bypass) ኢትዮ ቴሌኮም ማግኘት የሚገባውን 5 ሚሊዮን 43ሺ 108 ብር እንዲያጣ አድርጓል፡፡የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) በሀገራችን የሚፈጸሙ የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀሎችን በመቆጣጠርና በመከላከል ረገድ በተለያዩ ዘርፎች ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በጋራ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

http://www.fanabc.com/index.php/news/item/20932-%E1%89%A0%E1%89%B4%E1%88%8C%E1%8A%AE%E1%88%9D-%E1%88%9B%E1%8C%AD%E1%89%A0%E1%88%AD%E1%89%A0%E1%88%AD-%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE-%E1%89%B4%E1%88%8C%E1%8A%AE%E1%88%9D%E1%8A%95-%E1%8A%A85-%E1%88%9A%E1%88%8A%E1%8B%A8%E1%8A%95-%E1%89%A5%E1%88%AD-%E1%89%A0%E1%88%8B%E1%8B%AD-%E1%8B%AB%E1%88%B3%E1%8C%A3%E1%8B%8D-%E1%8C%8D%E1%88%88%E1%88%B0%E1%89%A5-%E1%89%A0%E1%8A%A5%E1%88%B5%E1%88%AB%E1%89%B5%E1%8A%93-%E1%89%A0%E1%8C%88%E1%8A%95%E1%8B%98%E1%89%A5-%E1%89%B0%E1%89%80%E1%8C%A3.html