አዲስ የኤ.ቲ.ኤም ማልዌር መገኘቱ ተገለጸ

ተመራማሪዎች ረቂቅ፣ ተለዋዋጭና ለመቆጣጠር አስቸጋሪ የሆነ የኤ.ቲ.ኤም ማልዌር ማግኘታቸውን አስታወቁ፡፡ የግኝቱ ባለቤቶች እንደገለጹት የኤ.ቲ.ኤም ቫይረሱ አዲስና ለመቆጣጠር አስቸጋሪ ከመሆኑም በላይ በቀጥታ የሚያጠቃው የባንክ ማሽንን ነው ብለዋል፡፡ማልዌሩ አላይንስ (Alince) የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን በአይነቱ የተለየና ከዚህ በፊት ከነበሩት የማልዌር ቤተሰቦች ጋር ሲነጻጸር ረቂቅ፣ ተለዋዋጭና ለመቆጣጠር አስቸጋሪ መሆኑን የግኝቱ ባለቤት ትሬንድ ማይክሮ ካምፓኒ ገልጿል፡፡ እንደ ካምፓኒው ገለጻ አዲሱ የኮምፒዩተር ቫይረስ በዋነኛነት የኤ.ቲ.ኤም ማሽንን የገንዘብ ዝውውር እንዲያቋርጥ እና የተሳለጠ አገልግሎት እንዳይሰጥ የማድረግ ጸባይ አለው ነው ያሉት፡፡ ከዚህ በፊት ከ9 የማያንሱ የኤ.ቲ.ኤም ማልዌር አይነቶች መኖራቸው የተጠቀሰ ሲሆን አሁን የተገኘው ግን ለዘርፉ ኢንዱስትሪ  ፈታኝ ሊሆን እንሚችል ተጠቁሟል፡፡ አጭበርባሪዎች የኤ.ቲ.ኤም ኮዱ ላይ አራት ዲጅት ቁጥሮችን በማስገባት ማሽኑ ትክክለኛ አገልግሎት እንዳይሰጥና ሲያስፈልግም ገንዘቡን ለመዝረፍ እንዲያመቻቸው የሚያግዝ የማልዌር አይነት ነው ተብሏል፡፡በመሆኑም ደንበኞችና ተጠቃሚዎች ይህን አውቀው የባንክ ማሽናቸው ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደረጉ እንደሚገባ የግኙቱ ባለቤቶች ሳይጠቅሱ አላለፉም፡፡

http://www.infosecurity-magazine.com/news/researchers-discover-new-lean-and/