የኢመደኤ አመታዊ የውስጥ የስፖርት ውድድር ተጀመረ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) በየአመቱ የሚያካሂደው የውስጥ የስፖርት ውድድር ታህሳስ 27 ቀን 2009 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ ተጀመረ፡፡ በየአመቱ በተቋሙ ውስጥ ያሉ ሰራተኞችንና አመራሮችን የሚያሳትፈው ስፖርታዊ ውደድር ዘንድሮም በተለያዩ የስፖርት ክንዋኔዎች በደመቀ ሁኔታ ተከፍቷል፡፡ በመክፈቻ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የተለያዩ አዝናኝ ውድድሮች የተከናወኑ ሲሆን፤ ከእነዚህ ፕሮግራሞች መካከልም የሰርከስ ትርዒቶች፣ የገመድ ጉተታ፣ የአጭር ርቀት ሩጫ ውድድር እንዲሁም የእግር ኳስ ውድድር ተካሂዷል፡፡ በየአመቱ የሚካሄደው የውስጥ የስፖርት ውድድር የተቋሙን ሰራተኞች እርስ በእርስ ከማቀራረብ ባሻገር ጤናማና በስፖርት የዳበረ ማህበረሰብ ለመገንባት አስተዋጽኦ እንዳለው በፕሮግራሙ ላይ ተገልጿል፡፡ ውድድሩ ሁሉንም በተቋሙ ውስጥ ያሉ የስራ ክፍሎችን እና ሰራተኞችን ባሳተፈ መልኩ የሚቀጥል ይሆናል፡፡