በአትክልት እና ፍራፍሬዎች ላይ የሚያጋጥሙ በሽታዎችን የሚያሳውቅ የሞባይል መተግበሪያ ተዋወቀ

በጀርመን ሀኖቨር ለአርሶ አደሮች በአትክልት እና ፍራፍሬዎች ላይ የሚያጋጥሙ በሽታዎችን የሚያሳውቅ የሞባይል ስልክ መተግበሪያ (Application) እንደተሰራ ዩሮ ኒውስ ይዞት በወጣው ዘገባ ገለጸ። መቀመጫውን በሃኖቨር ያደረገው ስታርትአፕ ፔት የተሰኘ ቡደን የሰራው እና "ፕላንቲክስ" የተባለው አዲሱ የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ በአትክልትና ፍራፍሬዎች ላይ የሚከሰቱ በሽታዎችን በመለየት ወዲያውኑ ለማከም ያስችላል ተብሏል። ይህ አዲስ የሞባይል መተግበሪያ የአትክልት እና ፍራፍሬዎችን ፎቶ አንስተን በምንሰጠው ጊዜ መረጃዎችን ተንትኖ የበሽታ አይነቶችን እና ደረጃቸውን ያሳያል ሲሉ የስታርትአፕ ፔት ስራ አስፈጻሚ ሲሞን ስትሬይ ገልጸዋል።    

http://www.euronews.com/2017/01/04/the-plant-doctor-app-helping-to-identify-plant-disease