ባንኮች የኤ.ቲ.ኤም ካርድን በእጅ ስልክ የሚተካ ቴክኖሎጅ ለተጠቃሚዎች ሊያቀርቡ ነው

አሁን ጥቅም ላይ የሚገኘው የኤ.ቲ.ኤም ካርድ አገልግሎትን የሚያሻሻል ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ ሊውል እንደሆነ ተገለፀ፡፡ ቴክኖሎጂው የደንበኞችን አካውንት ከእጅ ስልካቸው ጋር በማቆራኘትና አሰራሩን በመዘርጋት ገንዘባቸውን እንዲያዘዋውሩ የሚያድርግ በመሆኑ አንዳንድ የአሜሪካን ባንኮች ቴክኖሎጂውን መጠቀም እንደሚጀምሩ አስታውቀዋል፡፡ በአሜሪካን አገር የሚገኘው ጄፒሞርጋን ቼዝ ባንክ (JPMorgan Chase) ቴክኖሎጅውን በመቶ በሚቆጠሩ ማሽኖች ላይ ተግባራዊ ያደረገ ሲሆን በቅረቡ ከ6 ሺ በሚበልጡ ጠጨማሪ ማሽኖች ላይ ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አሳውቋል፡፡ ሌሎች ባንኮችም በፈረንጆቹ 2017 መጨረሻ ቴክኖሎጅውን ሙሉ በሙሉ እንደሚጠቀሙ ይፋ አድርገዋል፡፡ አዲሱ ቴክኖሎጂ የፋይናንሻል አሰራሩን ለማቃለል መልካም መሆኑ ቢመሰከርለትም የደህንነት ጉዳይ ግን አሳሳቢ መሆኑ ሳይጠቀስ አልታለፈም፡፡ ሪቻርድ ክሮን የተባሉት የዘርፉ ባለሙያ እንደገለጹት ቴክኖሎጂው ተግባር ላይ መዋሉ ከዚህ በፊት የነበረውን የባንክ አሰራር ይበልጥ የሚያሻሽልና አገልግሎቱን ቀላል ሊያደርገው እንደሚችል ተናግረዋል፡፡ ሆኖም ይላሉ ባለሙያው  ከደህንነት ጋር ተያይዞ ሊኖር በሚችለው ችግር ዙሪያ ግን ጥልቅ ውይይት መደረግ እንዳለበት ሳያስጠነቅቁ አላለፉም፡፡

https://www.nytimes.com/2017/02/13/business/dealbook/banks-look-to-cellphones-to-replace-atm-cards.html?_r=0