ታለቋ ብሪታንያ የሳይበር ደሕንነት ችግርን ለመቅረፍ አዲስ የትምርት ፕሮግራም ተግባራዊ ልታደርግ ነው

አገሪቱ ይህን የምታደርገው አዲስ ከተቋቋመው የሳይበር ክለብ ጋር በመተባበር ዜጎች ያለበቸውን የሳይበር ክህሎት ክፍተት ለመዝጋት እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ የአገሪቱ የባሕል፣ የሚዲያና ስፖረት መ/ቤት እንዳስታወቀው አሁን በፍጥነት ሥራው የሚጀምረው "ሳይበር ስኩል ፕሮግራም" በመባል የሚታወቅ ሲሆን ዕድሚያቸው ከ14 እስከ 18 ለሚደርሱ ዜጎች በሳይበር ደሕንነት ዙሪያ ስልጠናወችን የሚሰጥ ነው ተብሏል፡፡ የስልጠና ማዓከሉ ግንባታ 20 ሚሊዮን ዩሮ ይፈጃል ያለው መረጃው በ2021 ዓ.ም 5 ሺ 700 ተማሪችን ተቀብሎ እንደሚያሰለጥንና የሙከራ ጊዜውን ደግሞ በመጪው መስከረም እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡

በማዓከሉ አስተባባሪነት ስልጠናው መደበኛ ትምሕርትን በማይጎዳ መልኩ በሳምንት ለ4 ሠዓት ለሁሉም የአገሪቱ ተማሪዎች ለመስጠት የታቀደ ነው ያሉት የዲጂታልና የባሕል ሚኒስተር ደኤታ ማት ሀንኮክ ይህም ለበርካታ ተማሪዎች የዘሙኑን የሳይበር ክሕሎት እስከ 2ኛ ደረጃ የትምርት ፕሮግራም ባለው ጊዜ ውስጥ ጠንቅቀው እንዲያውቁ ይረዳቸዋል ብለዋል፡፡

አዲሱ ፕሮግራም ሃገሪቱን  ወደፊት ሊያጋጥማት የሚችለውን የሳይበር  ባለሙያዎች እጥረት ለመከላከል ከወዲሁ የቀረፀችው ብሔራዊ የሳይበር ደሕንነት ፕሮግራም አካል ነው፡፡

http://www.itproportal.com/news/the-uk-looking-to-close-the-cyber-security-gap-with-a-new-educational-programme/