በኢንፎርሜሽን ደህንነት ዙሪያ አሳሳቢ የሰው ሃይል እጥረት መኖሩ ተጠቆመ

The Center for Cyber Safety and Education በሚባል ተቋም የተጠና አንድ ጥናት እንዳመለከተው የኢንፎርሜሽን ደህንነት ባለሙያዎች እጥረት በ2022  ወደ 1.8 ሚሊዮን ከፍ እንደሚል ታውቋል፡፡ ይህም በማዕከሉ ከዚህ ቀደም በ2015 እጥረቱ 1.5 ሚሊዮን ገደማ ይደርሳል ተብሎ ከተገመተው የ20% ጭማሪ እንዳለው ተገልጧል፡፡

ጥናቱ በተጨማሪምወጣቱ ትውልድ ዘንድ ከፍተኛ ደሞዝ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ እንዳልሆነና ከዚያ ይልቅ ሙያዊ እድገትን መሰረት ያደረጉ እንደ ተሞክሮ ልውውጦች፣ የአመራር ስልጠናን፣ በኢንዳስትሪ ሁነቶች ላይ መካፈልን፡ እንዲሁም ሰርተፊኬት የሚያስገኙ የሙያ ስልጠናዎች በቀጣሪዎቻቸው ቢመቻቹላቸው እንደሚመርጡ አረጋግጧል፡፡ 

ለተጨማሪ፡- https://www.infosecurity-magazine.com/news/cyberworkforce-shortage-to/