ኢትዮጵያ ሳተላይት ለማምጠቅ አማካሪ ድርጅት መረጠች

 

ኢትዮጵያ የኮሙዩኒኬሽን ሳተላይት ለማምጠቅ ይረዳኛል ካለችው ከፈረንሳዩ ዩቴል ሳት ኩባንያ ጋር ውል ተፈራረመች፡፡ስራውን የሚያከናውነውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህነት ኤጀንሲን በመወከል ስምምነቱን የተፈራረመው የመንግስት ግⶵ እና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ነው፡፡ 

በስምምነቱ መሰረት ኩባንያው በቅድመ ትግበራ፣ በትግበራ እና በድህረ ትግበራ ወቅት አስፈላጊውን የቴክኒካል አገልግሎት ይሰጣል፡፡

ኢትዮጵያ የኮሙኒክሽን ሳተላይት ባለቤትነትን ማረጋገጧ የቴሌኮሙኒዩኬሽን፣ የሚዲያ፣ የጤና እና የትምህርት ተደራሽነትን በማሻሻል በኩል የጎላ ጠቀሜታ እንደሚኖረው በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል፡፡

አገሪቱ የኮሙኒኬሸን ሳተላይት ቴክኖሎጂ ባለቤትነትን ስታረጋገጥ በአሁኑ ወቅት ለሳተላይት ኪራይ የምታወጣውን ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ ዓመታዊ ወጪ ለማዳንም ያስችላታል፡፡

ከዚህ ቀደም የኢንፎርሜሽን መረብ ደህነት ኤጀንሲ ከመገናኛ እና ኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር ጋር በመሆን ለሳተላይቱ አስፈላጊ የሆነውን የፍሪኪዮንሲ እና የኦርቢታል ስሎት ለማግኘት የሚረዱ ሰነዶች አዘጋጅቶ ለአለም አቀፉ ቴሌኮሙዩኒኬሽን ማህበር(ITU) ጥያቄ አቅርቧል፡፡