ካስፐርስኪ የራሱን ኦፕሬቲንግ ሲስተም አስተዋወቀ

የሩሲያው የሳይበር ደህንነት እና አንቲ-ቫይረስ አልሚው ካስፐርስኪ ላብ (Kaspersky Lab) ከ14 ዓመታት ጉዞ በኋላ የራሱን ኦፕሬቲንግ ሲስተም አስተዋውቋል፡፡ በካስፐርስኪ ላብ የተለቀቀው አዲሱ ኦፕሬቲንግ ሲስተም (KasperskyOS) የሚባል ሲሆን የኮድ ስሙ KasperskyOS 11-11 እንደሆነም ተጠቅሷል፡፡ በፈረንጆቹ ህዳር 2016 ተቋሙ ከኔትዎርክ ጋር ለተያያዙ መሳሪዎች፣ ከኢንተርኔት ጋር ግንኙነት ላላቸው ዲቫይሶች እንዲሁም ለኢንዱስተሪ ሲስተሞች የሚውል የራሱን ለመረጃ ጥቃት የማይጋለጥ ኦፕራቲንግ ሲስተም (hackproof operating system) እንደሚያቀርብ ገልጾ እንደነበር የሚታወቅ ነው፡፡ ‘KasperskyOS ለሊኑክስ (Linux) ፣ዊንዶው (Windows) ፣ማክ (MacOS) እና መሰል ምርቶች  የሚስማማ እና አለማቀፋዊ  መሆኑም ተገልጧል፡፡
https://www.techworm.net/2017/02/kaspersky-launches-operating-system-14-years-hard-work.html