የአሜሪካ አየር ሃይል በከፍተኛ ሚስጥር የተያዘ መረጃ በስህተት መሹለኩ ተነገረ

የአሜሪካው አየር ሃይል በከፍተኛ ሚስጥር የተያዘ መረጃ መሹለኩ የተነገረ ሲሆን የመከላከያ መስሪያ ቤቱ መረጃ መሹለኩን ተከትሎም በከፍተኛ ሚስጥር የተያዙ የመከላከያ መስሪያ ቤቱ መረጃዎች እንዲሁም ከ4,000 በላይ የመከላከያ መኮንኖች የግል መረጃዎች የችግሩ ሰለባ እንደሆኑ ተነግሯል፡፡ ሚስጥራዊ መረጃው በኢንተርኔት የተጋለጠው ደህንነቱ ባልተጠበቀ መጠባበቂያ (backup) ውስጥ መረጃዎቹ በመቀመጣቸው መሆኑን MacKeeper የተባለው የደህንነት ተቋም ተመራማሪዎች ጠቁመዋል፡፡ በተፈጠረው ስህተትም የአየር ሃይል ከፍተኛ የጦር መኮንኖች የግል መረጃዎች፣ በጣም ከፍተኛ ሚስጥር ተብለው የተያዙ ዶክመንቶች እንዲሁም የደህንነት ማረጋገጫዎች መሹለካቸው ተነግሯል፡፡ ከሾለኩት መረጃዎች ውስጥም ከፍተኛ የጦር መኮንኖች እና መኮንኖች ስም፣ የስልጣን ደረጃ፣ መኖሪያ አድራሻ እና የማህበራዊ ዋስትና ቁጥሮች ይገኙበታል ተብሏል፡፡   

http://www.ibtimes.co.uk/us-air-force-leak-exposes-holy-grail-top-secret-data-including-details-over-4000-officers-1611404