ኮንግረሱ የኢንተርኔት ደህንነት ህግ እንዲቀየር ወሰነ

የአሜሪካ ምክር ቤት ከአንድ ዓመት በፊት በባራክ ኦባማ የስልጣን ዘመን ሥራ ላይ ውሎ የነበረው የኢንተርኔት ደህንነት ህግ እንዲቀየር መወሰኑን አስታወቀ፡፡ ከዚህ በፊት የነበረው ህግ የኢንተርኔት አቅራቢዎች ለሚያደርጉት ማንኛውም እንቅስቃሴ ተጠቃሚዎችን ማስፈቀድ እንዳለባቸው የሚደነግግ ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪም  የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች የራሳቸውን መረጃ ለመቆጣጠር የሚረዳና ለደህንነት የተሻለ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን ታላላቅ ካምፓኒዎችን የሚያበረታታ ነበርም ተበሏል፡፡ አሁን ስራ ላይ እንዲውል የተጠየቀው ህግ በተቃራኒው የኢንተርኔት አቅራቢዎች ያለምንም የግለሰብ ፈቃድ የሚፈልጉትን መረጃ ማሰራጨትም ሆነ መሰብሰብ እንዲችሉ የሚደነግግ ሲሆን ተወዳዳሪነትንና አቅርቦትን እንደሚጨምር ታምኖበታል፡፡ የተደረገውን ውሳኔ አንዳንድ የሕዝብ እንደራሴዎች በተለይም ከሪፐብሊካን ውጭ የሆኑት አበክረው ኮንነውታል፡፡

http://www.ibtimes.co.uk/us-house-votes-repeal-obamas-internet-privacy-protections-1614195