የሳይበር ጥቃት ዒላማ መሆኗ ያሳሰባት ጀርመን የሳይበር መከላከያ ቡድኖችዋን እያጠናከረች ነው

በያዝነው በፈረንጆቹ 2017 የጀርመን መከላከያ መስሪያ ቤት 300ሺህ የሚደርስ የሳይበር ጥቃት እንደተዘነዘረበት የመስሪያ ቤቱ የሥራ ኃላፊዎች አስታወቁ፡፡

ችግሩ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን ተከትሎ በመከላከያ መስሪያ ቤቱ የተቋቋመው የሳይበር ቡድን በፍጥነት በሃገሪቱ የመከላከያ ተቋማት እንዲስፋፋ ትዕዛዝ የተላለፈ ሲሆን  በምዕራባዊ ጀርመኗ ቦን ከተማ ብቻ በ250 የሰው ኃይል ሲንቀሳቀስ የነበረው የሳይበር ቡድን እስከ ሚቀጥሉት ሁለት ወራት በሌሎች የመከላከያ ቅርንጫፎች በመስፋፋት በ13ሺህ 500 የሰው ኃይል እንደሚያድግ ታውቋል፡፡

እንደ ሮይተር ገለፃ በአገሪቱ እየገዘፈ የመጣውን የሳይበር ጥቃት ለመከላከል ሃገሪቱ የሚኖራትን የሳይበር መከላከያ ጣቢያዎችን በፈረንጆቹ 2021 ከ14ሺህ በላይ ለማድረስ ዕቅድ መያዟም ተጠቁሟል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት የጀርመን ፓርሊያመንት በሰርጎ ገቦች መበርበሩ የሚታወስ ሲሆን በሌሎች የአውሮፓ አገራትም ሁኔታው እየተባባሰ መምጣቱን ዘገባው አሰስታውሷል፡፡

http://www.ibtimes.co.uk/german-military-hit-nearly-300000-cyberattacks-so-far-2017-cyber-chief-warns-1615085