በናይጄሪያ የሳይበር ደህንነት የግንዛቤ ማስጨበጫ ወር እየተከበረ ነው

በናይጄሪያ በጥቅምት ወር የሚከናወነው ብሔራዊ የሳይበር ደህንነት የግንዘቤ ማስጨበጫ ወር (National Cyber Security Awareness Month - NCSAM) እየተካሄደ መሆኑ itnewsafrica.com ዘገበ፡፡ እንደዘገባው የናይጄሪያ የኮሙዩኒኬሽን ኮሚሽን (NCC) በድረ-ገጹ ባስነበበው መረጃ መሰረት የሳይበር ደህንነት የግንዛቤ ማስጨበጫ ወር የማህበረሰቡን ንቃተ-ሕሊና ለማሳደግና ዜጎች ለሳይበር ደሕንነት ቅድሚያ ሰጥተው እንዲንቀሳቀሱ ትልቅ አጋጣሚ ይሆናል ተብሏል፡፡ ስለሆነም የኮሙዩኒኬሽን ኮሚሽን መስሪያ ቤቱ ጉዳዩን በሚችለው ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡ በዚህ የግንዛቤ ማስጨበጫ ወር በተለይ ዜጎች ወሳኝ መረጃዎችን በጥንቃቄ እንዲይዙ፣ የይለፍ ቃሎችን በየጊዜው እንዲያድሱ እና መሰል ዕውቀቶችን እንዲያስታውሱ ይጠቅማል ያለው ዘገባው ወሳኝ ለውጥም ያመጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡  

የሳይበር ደህንነት የግንዛቤ ማስጨባጫ ወር በአሜሪካው የአገር ውስጥ ደህንነት ተቋም (U.S. Department of Homeland Security - DHS) አባል ተቋማት መካከል በየዓመቱ የሚከበር ነው፡፡

http://www.itnewsafrica.com/2017/10/nigeria-ncc-backs-national-cyber-security-awareness-month/