ተመራማሪዎች በኢንተርኔት የሚነዙ የጥላቻ መልዕክቶችን የሚያስቀር ቴክኖሎጅ ማግኘታቸውን ገለጹ

ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣውን የኢንተርኔት ቀጥታ  ግንኙነት (online) የጥላቻ ንግግር ለማስቀረት አዲስ ቴክኖሎጂ መፍጠራቸውን በካናዳ የማክጊል ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች አስታውቁ፡፡ ችግሩ አደገኛ መሆኑን የተረዱት ተመራማሪዎቹ ለ10 ዓመታት ባደረጉት ያላሰለሰ ጥረት አሁን አመርቂ ውጤት ላይ መድረሳቸውን ibtimes ዘግቧል፡፡ ተመራማሪዎቹ እንደገለጹት የዚህ ግኝት ዋና ዓላማ በአሁኑ ሰዓት ለአገራት ስጋት የደቀነውን የጥላቻና ሀሰተኛ የኢንተርኔት መልዕክት የሚለይና በፍጥነት የሚያስወግድ መሆኑን አሳውቀዋል፡፡ ምንም እንኳ የጥላቻ ወሬዎችን ለይቶ ለማወቅ እንደየአገራቱ የሚለያይ ቢሆንም ጥቅም ላይ የሚውለው ግኝት በአካባቢው ዘየ መሰረት ጽንፈኛ መልዕክቶችን የመለየትና እንዳይተላለፉ የማድረግ አቅም አለው ተብሏል፡፡ አዲሱ የቴክኖሎጂ ውጤት እውን የሆነው የጥላቻ ወሬዎችን በተመለከተ የዓለም አገራት መሪዎች ከፍተኛ ውይይት እያደረጉ ባሉበት ወቅት ሲሆን፤ ይህን አስመልክተው የእንግሊዟ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ ለተባበሩት መንግስታት ያቀረቡትን ጥያቄና በዚህ ዙሪያ የአውሮፓ ሕብረት የደረሰበትን ስምምነት ዘገባው አስታውሷል፡፡

http://www.ibtimes.co.uk/researchers-develop-ai-that-can-put-end-online-hate-speech-1642291