ጌማልቶ ካምፓኒ አዲስ የኢንፎርሜሽን ደህንነት መጠበቂያ ፕላትፎርም ይፋ አደረገ

የኔዘርላንዱ የዲጂታል ደህንነት ኩባንያ ጌማልቶ (Gemalto) በማንኛውም ጊዜና ቦታ ኢንፎርሜሽን እዳይበረበር የሚከላከል አዲስ የደህንነት መጠበቂያ ፕላትፎርም ይፋ ማድረጉን አስታወቀ፡፡ አዲሱ የደህንነት መጠበቂያ በአጭር ጊዜ፣ በቀላል ወጭና ባልተወሳሰበ ዘዴ የኢንፎርሜሽን ምዝበራ ስጋትን ማስቀረት የሚችል እንደሆነም የጌማልቶ ኩባንያ የኢንተርፕራይዝና ሴኪዩሪቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ሴባስቲየን ካኖ ገልጸዋል፡፡ ፕላፎርሙ ከትናንሽ እስከ ታላላቅ ኩባንያዎች ድረስ በኢንፎርሜሽን ላይ የሚደርሰውን ስጋት ለመከላከል ያገለግላል ሲሉም ምክትል ፕሬዝዳንቱ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ፕላትፎርሙ ሁሉም የአይ.ቲ (IT) ውጤት በሆኑ ቁሳቁሶችና በቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ላይ ለመተግበር ታስቦ የተሰራ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

http://www.itnewsafrica.com/2017/11/first-of-its-kind-on-demand-security-platform-launched/