የደህንነት ተቋማት የሳይበር ጥቃት አጸፈዊ ምላሽ ሊወስዱ ይገባል ሲሉ የጀርመን ከፍተኛ የሳይበር ደህንት ሃላፊ ተናገሩ

የጀርመን የስለላ ተቋም ላይ ለሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶች አጸፋዊ እርምጃ መውሰድ የሚያስችል ሃላፊነት ሊኖር ይገባል ሲሉ አዲሱ የጀርመን የሳይበር ደህንነት ኤጀንሲ ፕሬዝዳንት ዚቲስ ተናገሩ፡፡ በተያዘው 2017 ዓመት መጀመሪያ አንስቶ የሳይበር ወንጀልን ለመዋጋት እና ሳይበር የሽብርተኞችን ግንኙነት መከታተል የሚያስችሉ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን መሳሪያዎችን በማበልጸግ ላይ መሆናቸውን ዚቲስ ጠቅሰዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ ይህን ሃሳብ ያቀረቡት ከፍተኛ የጀርመን ደህንት ሃላፊ ህግ አውጪዎች የሳይበር ጥቃቶች አጸፋዊ እርምጃ ("hack back") መውሰድ የሚስችላቸውን ስልጣን እንዲሰጣቸው ከጠየቁ ከወራት በኋላ ነው፡፡ በሚወሰደው እርምጃም ከውጭ መንግስታት የሚፈጸም ሳይበር ጥቃት አጸፋ መመለስን እንደሚካተት ነው የተነገረው፡፡ ይህን መሰል አጸፋዊ እርምጃዎች የመውሰድ ሃላፊነት በመንግስት ኤጀንሲዎች መኖር እንደሚገባውም ጠቅሰዋል፡፡

https://www.reuters.com/article/us-germany-cyber/german-cyber-agency-calls-for-authority-to-hack-back-spiegel-idUSKBN1DM1XU