በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ብቁ የሰው ሃይል እጥረት በተቋማት የሳይበር ወንጀል መከላከል ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳሳደረ ተገለጸ

 

የሳይበር ደህንነት ባለሙያዎች እንደሚገልጹት በተቋማት ላይ የሚፈጸሙ የሳይበር ወንጀሎችን ለመከላከል የተሻሻሉ የሙያ ስልጠናዎች ወሳኝ ድርሻ እንዳላቸው ይገልጿሉ፡፡ ከስራና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች እየወጡ ያሉ የቅርብ ጊዜ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ደግሞ በምህዳሩ ላይ 81 በመቶ በዲጂታል ደህንነት ዘርፍ የሰለጠኑ የሰው ሃይል ፍላጎቶች ቢያድግም የተጠየቁ እውቀቶችን አሟልተው የተገኙት 16 በመቶ ብቻ መሆናቸውን ያሳያሉ፡፡

በአሁኑ ሰዓትም የሰለጠነ የሰው ሃይል ፍሎጎት ጣራ የነካ ሲሆን ከሳይበር ችግሮች ጋር የተያያዙ ወጪዎች፣ የመድን ሽፋን ወጪዎች እንዲሁም በኮምፒውተሮች የተፈጸሙ ጥቃቶችን ለማጽዳት የሚፈጸሙ ክፍያዎች ማሻቀባቸውን የኮንሰልታንሲ 2ሴክ (consultancy 2-Sec) ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ቲም ሆልማን ያስረዳሉ፡፡

በእንግሊዙ የብሄራዊ የጤና አገልግሎት ተቋም የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሲስተም ላይ ዋናክራይ (Wannacry) በተባለው አጥፊ ሶፍትዌር የተፈጸመው ጥቃት በዘርፉ ያለው የሰው ሃይል እጥረት ብቻ ሳይሆን የሰለጠነ የሰው ሃይል እጥረት የፈጠረው ክፍተት መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

በመሆኑም በዘርፉ ያለውን የሳይበር ወንጀል ለመከላከል የሰለጠነ እና ብቁ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያዎችን ማሟላት በአስቸኳይ ችግሮችን ለመቋቋም ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለቸው ተጠቁሟል፡፡

https://www.theguardian.com/technology/2017/dec/25/lack-of-it-staff-leaving-companies-exposed-to-hacker-attacks