ፌስቡክ የግለሰቦችን ዳታ ያለፈቃዳቸው መበርበሩን አመነ

የፌስቡክ ኩባንያ ሰሞኑን 50 ሚሊዮን የሚጠጉ ግለሰቦች ዳታ ያለነሱ ፈቃድ መበርበሩንና ለአንድ የፖለቲካ አማካሪ ጥቅም ላይ ውሏል በሚል የደረሰበትን ውንጀላ ማመኑን አስታወቀ፡፡

የፌስቡክ መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚው ማርክ ዙከርበርክ ለሲ.ኤን.ኤን እንደተናገሩት ኩባንያው ስሕተት መፈጸሙንና ለተፈጠረው ችግርም ይቅርታ መጠየቁን ዘገባው አብራርቷል፡፡ ለኮንግረንስ ሁኔታውን ከመናገራቸው ቀድመው ለሚዲያ ማሳወቃቸው እንዳስደሰታቸው የተናገሩት ስራ አስፈጻሚው ከዚህ በኋላ ተመሳሳይ ስህተቶች ላለመድገም ጠንክረን እንሰራለን ብለዋል፡፡ ፌስቡክ 50 ሚሊዮን የሚሆኑ ደንበኞቹ ያለፈቃዳቸው የግል ዳታቸው ስለመበርበሩ የጠቀሰው ዘገባው ተመሳሳይ ስጋቶች በዓለም ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳይ ላይ እያስከተሉ የሚገኙት ተጽኖ ቀላል እንዳልሆነም ታውቋል፡፡

ችግሩ እየገዘፈ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞም በርካታ የኩባንያው የአክሲዎን ባለድርሻዎች እየወጡ መሆኑን የሲን.ኤን. ኤን ዘገባ ያመለክታል፡፡ 

http://money.cnn.com/2018/03/21/technology/mark-zuckerberg-cnn-interview/index.html