ፓፑዋ ጊኒ የፌስቡክ አገልግሎትን ለአንድ ወር ልታቋርጥ ነው

አገሪቱ ፌስቡክን ለማቋረጥ የተገደደችው በሀሰት በሚነዛ ወሬ ዜጎቿ  ለአደጋ እየተጋለጡ መሆኑን ተከትሎ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ እንደ ዘጋርዲያን ዘገባ የአገሪቱ መንግስት ይህን ለማድረግ የወሰነነበት ዋነኛው ምክንያት የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመለየትና የማስተካከያ እርምጃ ለመውሰድ  ነው፡፡  መንግስት በፌስቡክ የሚደርሱ ጉዳቶችን ሲመረምር መቆየቱን ያረጋገጠው ዘገባው የትስስር ገጹ መቋረጥ እየተከሰተ ያለውን የግለሰቦች ደህንት ችግር ለማስቀረትም አይነተኛ ሚና ይኖረዋል ተብሏል፡፡ ከዚህም ሌላ ፌስቡክ እያደረሰ የሚገኘውን ተጽዕኖ ለመከላከል ሌሎች አገራት በማሕበራዊ መገናኛዎች ላይ የሚከተሉትን አሰራር እያማተረ ሲሆን አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ መዘጋጀቱንም የአገሪቱ መንግስት  አስታውቋል፡፡  

ፌስቡክ በፖለቲካዊና ማሕበራዊ ጉዳይ ላይ ጣልቃ ገብቷል በሚል የተለያዩ አገራት ጠበቅ ያለ ትችት ከማቅረባቸውም በላይ የሕግ ቁጥጥር እያደረጉ መሆኑ ይታወሳል፡፡   

https://www.theguardian.com/world/2018/may/29/papua-new-guinea-facebook-ban-study-fake-users