የሳይበር ደሕንነት ስጋት ለኩባንያዎች ፈተና ሊሆን ይችላል ተባለ

በቀጣዮቹ ዓመታት የኩባንያዎች ስጋትና ኪሳራ የሳይበር ደህንነት ችግር ሊሆን እንደሚችል ተጠቆመ፡፡ የአውስትራሊያው የደህንነት ተቋም (ASX) በወሰደው ጥናት መሰረት 80 ከመቶ የሚሆኑ ኩባንያዎች የሳይበር ወንጀል ቀዳሚ ስታቸው ሊሆን እንደሚችል ማረጋገጡን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ እንደ ጥናቱ ገለጻ ችግሩን ለመከላከል የተቋማቱ አመራሮች አስፈላጊውን የመከላከል እርምጃ በአፋጣኝ የማይወስዱ ከሆነ ሁኔታው ከፍተኛ ዋጋ ያስከፍላል ተብሏል፡፡ ችግሩን ለመከላከል በተለይ የሳይበር ስጋቱን መቋቋም (cyber resilient) ዋነኛው አማራጭ ነው ያለው ዘገባው በችግሩ ዙሪያ የተለየ ጥንቃቄ እንደሚያሻውም ጥናቱ አስገንዝቧል፡፡

ከዚህ አንጻር እያንዳንዱ የኩባንያ ሰራተኞችና አመራሮች ስለ ሳይበር እና ዳታ ደሕንነት የተጠናከረ ዕውቀትና ግንዛቤ ሊኖራቸው ይገባል ተብሏል፡፡  

https://www.uq.edu.au/news/article/2018/06/cyber-security-new-challenge-company-directors