የሳይበር ወንጀልን ለመከላከል ዜጎችን ማስተማር ትልቁ አማራጭ እንደሆነ ተገለጸ

በሳይበር ወንጀልና ደህንነት ዙሪያ ለዜጎች የተጠናከረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት መስጠት ችግሩን ለመከላከል  አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች አስታወቁ፡፡ ሮይተርስ ይዞት በወጣው ዝርዝር ዘገባ እንደተመለከተው በአሁኑ ወቅት በሳይበር ወንጀለኞች እየተሰነዘረ የሚገኘው ጥቃት በዜጎችና በአገራት ላይ የሚያስከትለው ኪሳራ ከምናስበው በላይ ነው ተብሏል፡፡ ችግሩ ከኪሳራም አልፎ በተቋማትና በዜጎች መካከል አለመተማመንን በማስፋፋት ለየአገራቱ ከፍተኛ አደጋ መደቀኑንም ዘገባው አስታውሷል፡፡

ስጋቱን ለማስወገድ ታዲያ ስለ ሳይበር ዜጎችን ማስተማር (Educating the Public about Cybersecurity) ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው ሲሉ ምሁራኑ አስምረውበታል፡፡

https://www.reuters.com/article/idUSWAOANHESGJHY1858