ጎግል በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን የአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ምርምር ማዕከል ሊከፍት ነው

ሰኔ 7/2010 ዓ.ም፡ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን የአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ምርምር ማዕከል በፈረንጆቹ 2018 መጨረሻ በጋና መዲና አክራ ሊከፍት እንደሆነ ጎግል ኩባንያ አስታውቋል፡፡ የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ ሱንዳር ፒካ እንደገለጹት የምርምር ማዕከሉ በአፍሪካ መከፈቱ ከአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ጋር ተያይዘው በአፍሪካ ለሚካሄዱ ምርምሮችና ግኝቶች ከፍተኛ ሚናን ይጫወታል ብለዋል፡፡

የምርምር ማዕከሉ በጋና ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የምርምር ማዕከላት እና የፖሊሲ አውጪዎች ጋር በቅንጅት እንደሚሰራና በአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ ዘርፍ ያለውን አቅም አሟጦ ለመጠቀም እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡

ጎግል ተመሳሳይ የአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ የምርምር ማዕከሎች በፓሪስ፣ ቴል አቪቭ እና ሳን ፍራንሲስኮ እንዳሉት ቢቢሲ ይዞት በወጣው መረጃ ጠቅሷል፡፡

https://www.bbc.com/news/live/world-africa-44436768?ns_mchannel=social&ns_source=twitter&ns_campaign=bbc_live&ns_linkname=5b214206dbaa490683f8f4f9%26Google%27s%20first%20African%20AI%20research%20centre%20to%20open%20in%20Ghana%26&ns_fee=0#post_5b214206dbaa490683f8f4f9