የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር የሳይበር ጉዳትን እንከላከል ሲሉ ለዓለም አገራት ጥሪ አቀረቡ

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታኒያሁ የሳይበር ስጋትን ለመከላከል በዓለም ዙሪያ የሚገኙ መንግስታት ጥረት ያስፈልጋል አሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በአገሪቱ ላይ በተዘጋጀ የሳይበር ሳምንት ኮንፈረንስ (Cyber Week Conferenc) ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ነው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት፡፡ ሮይተርስ እንደዘገበው ሳይበር የተለያዩ ጥቅሞች እንዳሉት ቢታወቅም እያስከተለ ያለውን የጎንዮሽ ችግር ለመመከት የዓለም ማሕበረሰብ መተባበር እንዳለበት ተጠቁሟል፡፡

የተለያዩ አገር መንግስታት የሣይበር ስጋትን ለመከላከል ልዩ ልዩ እርምጃዎችን እየወሰዱ መሆናቸው ይታወሳል፡፡   

https://www.reuters.com/article/us-israel-cyber-netanyahu/israels-netanyahu-warns-of-cyber-risks-that-can-down-fighter-jets-idUSKBN1JG1CL