ብሪታንያ አዲስ የሳበር ማበልጸጊያ ማዕከል ከፍታለች

ታላቋ ብሪታንያ በለንደን ከተማ አዲስ የሳይበር ማበልጸጊያ ማዕከል መክፈቷንን የታላቋ ብሪታንያ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አስታወቁ፡፡ በመንግስት በተበጀተ 13.5 ሚሊዮን ፓውንድ የተገነባው ማዕከሉ በዲጅታል ቴክኖሎጂው ዘርፍ የሚከናወነውን ተግባር ደህንነቱን  ለማረጋገጥ የሚያግዝ ነው ተብሏል፡፡ በአገሪቱ መንግስት አስፈላጊና ወሳኝ የተባለለት ይህ ተግባር ብቃት ያላቸው ኩባንያዎችና ግለሰቦች የሳይበር ደሕንነት ቴክኖሎጅን የሚያበለጽጉበት ቦታ ነው፡፡ የነገው ትውልድ ሕልውና በዲጅታል ቴክኖሎጅ ላይ የተመሰረተ ነው ያሉት የስራ ኃላፊዎቹ ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚከሰተውን የሳይበር ደሕንነት ችግር ለመቆጣጠር ደግሞ ከወዲሁ መሰረት ማስያዝ ስለሚያስፈልግ ማዕከሉ መከፈቱን አብራርተዋል፡፡

የሳይበር ማበልጸጊያ ጣቢያው አገሪቱ በዓለም ላይ በዘርፉ ከፍተኛ ልሕቀትን ለማግኘት እያደረገች የሚገኘውን ጥረት ለማሳለጥም አይነተኛ ሚና ይኖረዋል ተብሏል፡፡

https://www.computerweekly.com/news/252443659/London-cyber-innovation-centre-opens