የጀርመን ባንኮች አሰራራቸውን በምጡቅ ቴክኖሎጅ ሊያዘምኑ ነው

በአገር ጀርመን የሚገኙ ባንኮች በቢሊዮን ዶላር የሚገመት ገንዘብ ኢንቨስት በማድረግ አሰራራቸውን በምጡቅ ቴክኖሎጅ ሊያዘምኑ መሆኑን አስታወቁ፡፡ የአገሪቱ ባንኮች ይህን የሚያደርጉት በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት የአሕጉሩን የባንክ ኢንዱስትሪ ከፍ ለማድረግና ልቆ  ለመገኘት ታልሞ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ ብሉምበርግ በድረ-ገጹ እንዳሰፈረው ባንኮቹ ይህን ለማስፈጸም እስከ ፈረንጆቹ 2020 ድረስ 7 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት የሚያደርጉ ሲሆን ሲስተሙ ወደ ስራ ሲገባም ከፍተኛ ትርፍ ያስገኛል ተብሏል፡፡

አሰራሩ መዘመኑ የአገሪቱ ባንኮች ከአውሮፓ አልፈው በዓለማቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እና አሸናፊ ለመሆንም አይነተኛ ሚና እንዲኖራቸው ይረዳል ተብሏል፡፡

https://www.bloomberg.com/news/articles/2018-06-27/german-banks-betting-billions-of-euros-on-tech-to-boost-revenue