ዋትስአፕ የሃሰት ወሬዎችን ለመከላከል ከመንግስታት ጋር ተቀራርቦ እንደሚሰራ ገለጸ

ዋትስአፕ በሕንድ አገር የሃሰት ወሬዎችን ለመከላከል ከመንግስት ጋር ተቀራርቦ ሊሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡  ሮይተረስ እንደዘገበው የፌስቡክ ኩባንያ አካል የሆነው ዋትስአፕ እየተሰራጨ ያለውን የሀሰት ወሬ ለመቀልበስ ከመንግስት በተጨማሪ በአገሪቱ ከሚገኙ ከቴክኖሎጅ ተቋማትና ከሲቪል ማሕበራት ጋር በጋራ እንደሚሰራ አስታውቋል፡፡ ኩባንያው ለአገሪቱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በደብዳቤ እንደገለጸው በአገሪቱ ላይ ስር-ነቀል ለውጥ ለማምጣት እንደሚንቀሳቀስ እና ማንኛውንም አላስፈላጊ መልዕክት እንዳይሰራጭ ለማድረግ ቃል ገብቷል፡፡

ድርጅቱ ይህን ያለው የሕንድ የአይ.ቲ ሚኒስትር በዋትስአፕ አማካኝነት በአገሪቱ ላይ እየተሰራጨ ያለውን የሀሰት ወሬ ጥያቄ ማቅረቡን ተከትሎ ነው፡፡

https://www.reuters.com/article/us-whatsapp-india-fakenews/whatsapp-to-india-need-partnership-with-government-civil-society-to-curb-spread-of-false-messages-idUSKBN1JU0HO