የቻይና የመረጃ ደህንነት ህግ እና የቴክኖሎጂ ኩባንያዎቿ አጣብቂኝ

አዲስ አበባ፤ ነሃሴ 17/2010

ቻይና ተግባራዊ ካደረገቻቸው የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ጋር የተያያዙ ህጎች ጥብቅ ሲሆኑ በሃገሯ ያሉ ኩባንዎች እና ዜጎች ሃገሪቱ በምታከናውነው የወንጀል የምርመራ ተግባራት ከመንግስት ጋር እንዲተባበሩ የሚያዝ ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም ቻይና የቴክኖሎጂ ተቋማት በቻይና የስለላ ሂደት ውስጥ ያሉ ናቸው በሚል የቻይና ምርቶች እንደ አሜሪካ እና መሰል ሃገራት ገደቦች ተጥሎባቸዋል፡፡ አሁን ላይ ደግሞ አውስትራሊያ የቻይናውን የቴሌኮም ኩባንያ ሁዋዊ ሃገሪቱ ልትዘረጋ ያሰበችውን የ5ጂ የሞባይል ኔትዎርክ ግብአቶች እንዳያቀርብ እገዳ ጥላለች፡፡ አውስትራሊያ ከፍተኛ የንግድ አጋሯ በሆነቸው የቻይና ኩባንያዎች ላይ ይህን አይነት ውሳኔዎችን ለመወሰን ከባድ ቢሆንባትም ከደህንነት ኤጀንሲዎች በቀረቡ ማስጠንቀቂያዎች እና የቻይና ስውር እጅ በሃገሯ ፖለቲካ ውስጥ ጣልቃ መግባቱን ተከትሎ ነው፡፡ ይህ ሁኔታም ጥሩ የነበረውን የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት እያሻከረው መምጣቱን ሲሆን ሃገሪቱ ከደህንነት ስጋት ጋር በተያያዘ መሆኑም ለዚህ ውሳኔ መብቃቷ ተጠቁሟል፡፡

ሃገራት የሳይበር ደህንነታቸውን ለማረጋገጥ በሃገር በቀል ምርቶች መጠቀም እና አቅምን ማሳደግ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጠው ተግባር ነው፡ አውስትራሊያም የሃገሯን የመገናኛ ስርዓቶች ደህንነታቸው የተጠበቁ እንዲሆኑ ከፍተኛ የሚባል በጀቶችን መድባ እየተንቀሳቀሰች ትገኛለች፡፡ አውስትራሊያ ከዚህ ቀደም የሁዋዌ ምርት የሆነውን የፋይበር ኦፕቲክስ ወደ ሃገሯ እንዳይገባ ማገዷ የሚታወስ ነው፡፡

https://www.reuters.com/article/us-australia-china-huawei-tech/australia-bans-chinas-huawei-from-mobile-network-build-over-security-fears-idUSKCN1L72GC