ኢንጂነር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ዋ/ሥራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ

 

 

አዲስ አበባ፤ ነሃሴ 17/2010 ዓ.ም

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) ም/ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ኢንጂነር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ዋ/ሥራ አስፈፃሚ ሆነው ተሹመዋል፡፡ የኢመደኤ አመራርና አባላት ስኬታማ የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው ይመኛሉ፡፡ 

 

የሥራ ልምድ

 • ከ1991 ዓ.ም ጀምሮ የኢፌዲሪ የመከላከያ ሰራዊት አባል በመሆን እስከ ሌተናል ኮሎኔል ማዕረግ ደረጃ ደርሰዋል፡፡
 • ከ1996-1998 ዓ.ም የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ በአስተማሪነት አገልግለዋል፡፡
 • 1998 ዓ.ም ኢመደኤ ሲቋቋም ከተመረጡት ሙያተኞች አንዱ በመሆን እስከ የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው እስከተሾሙበት ጊዜ ድረስ በኤጀንሲው የተለያዩ የስራ ኃላፊነት ደረጃዎች ሰርተዋል፡፡
 • በመጨረሻም የኢመደኤ ም/ዋና ዳይሬክተር ሆነው በክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ ተሹመው ላፉት አራት ወራት አገልግለዋል፡፡
 • ከቋሚ ስራቸው ጎን ለጎን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በመዘዋወር ሲያስተምሩ ቆይተዋል፡፡
 • ከ2007- 2009 ዓ.ም በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሚመራ የሃገር አቀፍ የምርምር ካውንስል ቴክኒካል አማካሪ አባል በመሆን አገልግለዋል፡፡
 • ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ የሳይበር ታለንት ልማት ኢንስቲትዩት ቦርድ ሰብሳቢ በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡
 • በ2008 ዓ.ም በሃገር ደረጃ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር በተዘጋጀ ችግር ፈቺ የምርምር ውጤት ውድድር ተወዳድረው በማሸነፋቸው የ3.9 ሚሊዮን ብር ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
 • ዶ/ር ኢንጂነር አብርሃም የጥናትና ምረምር ውጤቶቻቸው በተለያዩ ዓለም አቀፍ ጆርናሎች አሳትመዋል፡፡ የሁሉም የጥናት ውጤቶቻቸው ትኩረት ሃገራዊ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትንና ባለቤትነትን ማረጋገጥ የሚያስችሉ እና በተለይ ደግሞ የኤሌክትሪክ ኃይል አመራር ደህንነትና ሞደርናይዜሽን ስርዓቶች ምን መምሰል እንዳለባቸው የሚያስቀምጡ ናቸው፡፡

 

የትምህርት ደረጃ

የመጀመሪያ ዲግሪ

በመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ቢሾፍቱ

 • በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ የሙያ መስክ
 • በኤሌክትሪካል ፓወር ኢንጂነሪንግ ስፔሻላይዜሽን
 • በ1996 ዓ.ም በእጅግ ከፍተኛ ማዕረግ ተመርቀዋል

 

ሁለተኛ ዲግሪ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

 • በኤሌክትሪካል ኮምፒውተር ኢንጂነሪንግ የሙያ መስክ
 • በኤሌክትሪካል ኮንትሮል ኢንጂነሪንግ ስፔሻላይዜሽን
 • በ2000 ዓ.ም በከፍተኛ ማዕረግ ተመርቀዋል

 

ሶስተኛ ዲግሪያቸውን

ቡላካን ስቴት ዩኒቨርስቲ (ፊሊፒንስ)

 • በቢዝነስ አድሚስትሬሽን የሙያ መስክ
 • በኤሌክትሪካል ኢነርጂ ማናጅመንት የምርምር ዘርፍ
 • በ2007 ዓ.ም አጠናቀዋል

 

አራተኛ ዲግሪያቸውን

ፔኪንግ ዩኒቨርስቲ ቻይና (Post Doctorial)

 • በሪሞት ሴንሲንግና ካርቶግራፊ የሙያ መስክ
 • በሀገራዊ ገቨርናንስና አርክቴክቸር የምርምር ዘርፍ በማጠናቀቅ  ላይ ናቸው፡፡