ይህች አነስተኛ ጥቁር ፍላሽ መሰል ሞደም የአፍሪካን ኢንተርኔት የመለወጥ ብቃት እንዳላት ሲኤንኤን ዘገበ

ይህች አነስተኛ ጥቁር ፍላሽ መሰል ሞደም የአፍሪካን ኢንተርኔት የመለወጥ ብቃት እንዳላት ሲኤንኤን ዘገበነገሩ እንዲህ ነው ፡ - ኬንያውያን በፈጠራ ስራ ላይ በማተኮራቸው የኢንተርኔት ግንኙነትን በመላው አፍሪካ ሊያሻሽል የሚችል ግኝት ሰርተዋል፡፡ በ2013 የተመሰረተው ቢአርሲኬ የተባለው ፕሮጀክት የተለያዩ የቴክሎጂ ፈጠራዎች በተማሪዎች የሚሰራበት ሲሆን በማዕከሉ አዲስ የፈጠራ ውጤት የሆነ የኮኔክሽን እና የሃይል እጥረት ላለባቸው አካባቢዎች የሚያገለግል ሞደም ሰርተው አቅርበዋል፡፡

ይህችን የፈጠራ ስራ ለየት የሚያደርጋት በሎካል የኮምፒውተሮች ግንኙነት መሃል መስራቷ፤ ዋይፋይ ፤ 3ጂ እና 4ጂ ኔትወርክ መጠቀሟ ፤ እንዲሁም ሃይል በሚቋረጥበት ወቅት ለ8 ሰዓታት ያህል በባትሪ መስራቷ ነው ሲል ዘገባው አስነብቧል ፡፡ 
ይህች የቴክኖሎጂ ውጤት በአፍሪካ ላለው የኢንተርኔት ችግር ብሎም የሃይል መቆራረጥ አይነተኛ አማራጭ እንደምትሆን ሲኤንኤን በዘገባው አስነብቧል፡፡ 
ለበለጠ መረጃ ይህንን ሊንክ ይጫኑ፡ - http://edition.cnn.com/…/kenya-tech-startup-inte…/index.html