ጎግል አዲስና ለየት ያለ አገልግሎት የሚሰጥ የማፈላለጊያ ገጹን ይፋ አድርጓል።

ኪድል የተሰኘው አዲሱ ማፈላለጊያ ገጽ አቀራረቡ የጎግልን አይነት ሲሆን፥ በይዘት ግን የተለየ ነው።

ተጠቃሚዎች ወደ ገጹ ገብተው የፈለጉትን እንዲያገኙ ሲያደርግ፥ ከጎግል ለየት ያለ መንገድን ይከተላል።

አላስፈላጊና በቤተሰብ ደረጃ እንዲሁም ህጻናት ሊያዩት የማይገባቸውን ገጾች በዚህ ድረ ገጽ ማግኘት አይታሰብም።

ወሲብ ነክ የሆነ ማንኛውንም አይነት መረጃ ድረ ገጹ ያግዳል፤ ምናልባት ተጠቃሚው ቢጠይቅ እንኳን አያገኘውም።

ገጹ በዋናነት ህጻናትን ታሳቢ ያደረገና ህጻናት ሊያገኙት የሚገባን መረጃ ብቻ የሚያቀርብ ነው።

ይህም ለቤተሰብ ትልቅ እፎይታ ነው ተብሏል፤ ህጻናትና ታዳጊዎችን ከአላስፈላጊ ነገሮች ይጠብቃልና።

ታዋቂ እና ዝነኛ ሰዎችን ለማወቅ በሚደረግ ጥረት ከግላዊ መረጃዎቻቸው የዘለለ የህይዎት ዘይቤያቸውንና የሚያደርጓቸውን ነገሮች ይህ ገጽ ለህጻናቱ አያቀርብም።

በዚህ የማፈላለጊያ ገጽ ለቤተሰብ እና ለህጻናት የሚሆኑ ጤነኛ መረጃዎችን እንጅ ሌሎች ነገሮችን እንደማይፈቅዱም ነው የተገለጸው።

እናም ይህ አዲስ ገጽ ቀለል ያለ ይዘትና ለህጻናት የሚሆን አይነት አቀራረብ ያላቸውን መረጃዎች ብቻ ይፈቅዳል።

በዚህ ገጽ ላይ የሚሰፍሩ የመጀመሪያዎቹ ሶስት መረጃዎች ለህጻናት ሲሆኑ፥ ከዛ ቀጥሎ ያሉት ተከታታይ አራት መረጃዎች ቀለል ባለ አገላለጽ የቀረቡ እና ለእድሜያቸው የሚመጥኑ ጽሁፎች ይሆናሉ ተብሏል።

ከዚህ በኋላ ያሉት ደግሞ ለአዋቂዎች የሚሆኑ እና ጤነኛ መረጃዎች ብቻ እንደሆኑም ተገልጿል።
ለበለጠ መረጃ ይህንን ሊንክ ይጫኑ ፡- news.sky.com