ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ 11ኛውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በደመቀ ሁኔታ አከበረ

11ኛው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን "ህገ-መንግስታችን ለዴሞክራሲያዊ አንድነታችን ለህዳሴያችን" በሚል መሪ ቃል የኤጀንሲው አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፡፡ ሕዳር 29 ቀን 2009 ዓ.ም በፓናል ውይይት በተከበረው በዚህ በዓል ላይ "የኢትዮጵያ ፌዴራሊዝም አግባብነትና ልዩ ባህሪያት" እንዲሁም "የማቴሪያሊዝም ፓራዲያም እና ኪራይ ሰብሳቢነት" በሚል ርዕስ የኤጀንሲው ወጣት ሰራተኞች ባቀረቡት የውይይት ሃሳብ ዙሪያ  ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡ በመጨረሻም የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክቶር ሜ/ጄ ተክለብርሃን ወ/አረጋይ ለኤጀንሲው ሰራተኞች እና አመራሮች ባስተላለፉት መልዕክት የኤጀንሲው ማህበረሰብ በምክንያት የሚያምንና የአለምን ነባራዊ ሁኔታ መገንዘብ የሚችል እንዲሁም ነገሮችን በሁለት ጽንፍ ብቻ ከመመልከት ልዩነቱን ተንትኖ በማየት የሚገነዘብ እና አማራጭ ሃሳቦችን ማቅረብ የሚችል መሆን እንደሚገባው አስገንዝበዋል፡፡