የ130 የአለማችን ዝነኞች (Celebrities) የኢሜል አካውንት በሰርጎ ገብ ተጠቃ

የ23 አመቱ የበሀሚን ሰው የ130 ዝነኞችን እና አትሌቶችን የኢሜል አድራሻ ሀክ በማድረግ እና ለገበያ ያልቀረቡ ፊልሞችን ፣ የቲቪ ስክሪፕቶችን (TV scripts) ፣ የግል ምስጢራዊ ሰነዶችን ፣ ምስሎችን (explicit images) ገና ያልተለቀቁ አልበሞችን በመስረቅ ወንጀል ተከሶ ታስሯል ፡፡
እነኚህን የተሰረቁ ስክሪፕቶች (stolen scripts) አሎንዞ ናውልስ በመባል የሚታወቅ የመረጃ መንታፊ (hacker) ለአንድ ታዋቂ የራዲዮ ሆስት ለሽያጭ ማቅረቡ የታወቀ ሲሆን ይህ ስሙ ያልተጠቀሰው የሬዲዮ ጣቢያም ለአሜሪካው ሆም ላንድ ሴኩሪቲ መረጃውን በማቀበሉ በስውር ምርመራ ሲደረግባቸው ቆይቷል፡፡ በመረጃ መንታፊዎቹ ተሰርቀው ለሽያጭ የቀረቡት የሶስት ኮሜዲ ፊለሞች ስክሪፕት ፣ የቴሌቪዥን ሾው (ትዕይንት)፣ የአክተሮች እና አትሌቶች ማህበራዊ ዋስትና ቁጥር፣ የዝነኞች ስልክ ቁጥር እና ኢሜል ናቸዉ፡፡ 
ሀከሩ በቁጥጥር ስር የዋለውም እነኚህን መረጃዎች በ80,000 የአሜሪካን ዶላር ለመሸጥ በሀማስ (Bahamas) ማንሃታን (Manhattan) ባረፈበት ጊዜ ነበር ፡፡ መረጃው ስለተመነተፈባቸዉ ዝነኞች ማንነት ግን ያለው ነገር የለም ፡፡.