ጉግል በ2016 ከ900 ሚሊዮን በላይ የተጭበረበሩ ፍለጋዎችን እንዳገደ ገለጸ

ጉግል በፈረንጆቹ 2016 ብቻ የማታለል ይዘት ያላቸውን ከ900 ሚሊዮን በላይ ፍለጋዎችን ማስወገዱን ገለጸ፡፡ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ትክክለኛ ያልሆኑና ህገ-ወጥ ፍለጋዎች እንደደረሱት የገለጸው ተቋሙ ከእነዚህ መካከልም ከ900 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑትን በተሳካ ሁኔታ ማስወገድ ችያለሁ ብሏል፡፡ ጉግል በማጭበርበር ተግባር ላይ የተሰማሩ ድረ-ገጾች አገልግሎታቸው ተደራሽ እንዳይሆኑ በማድረግ ደረጃ የተወሰኑ እርምጃዎችን እንደተራመደ ተናግሯል፡፡ ተቋሙም ከፊልምና ሙዚቃ ካምፓኒዎች እና አዘጋጆች በተደጋጋሚ በማጭበርበር እና የአእምሯዊ ንብረት ባለቤትነትን ባላከበረ መልኩ የተሰማሩ ሊንኮችና ድረ-ገጾች እንዲወገዱ ተደጋጋሚ ግፊት እንዳደረጉበት የገለጸ ሲሆን፤ በ2016 የአእምሯዊ ንብረት ባለቤትነት ባላከበረ መልኩ ሲንቀሳቀሰ ነበረ ያለውን ኪክአስ ቶሬንት (KickassTorrents) ድረ-ገጽ ከመዘጋቱ ጋር ተያይዞ የሙዚቃና የፊልም ኢንዱስትሪዎች የተሻለ የማሸነፍ እድል ተፈጥሮላቸው ነበር ብሏል፡፡


http://www.ibtimes.co.uk/over-900-million-pirate-links-were-removed-google-search-results-2016-1598786