በፈረንጆቹ 2020 1.9 ቢሊዮን የባንክ ደንበኞች የባዮሜትሪክ ቴክኖሎጂን ይጠቀማሉ፡ሪፖርት

 

አዲስ አበባ፡መስከረም 16/2011፡- በሚቀጥሉት 2 ዓመታት ውስጥ ብቻ ከግማሽ ቢሊዮን በላይ ህዝብ ለባንክ አገልግሎት የባዮሜትሪክ (Biometrics) የደህንነት ማረጋገጫ ቴክኖሎጂን ተግባራዊ እንደሚያደርጉ በቅርብ እየወጡ ያሉ ሪፖርቶች ይጠቁማሉ፡፡

መቀመጫውን በለንደን ያደረገው ጉዲ የባዮሜትሪክ ኩባንያ ባንክ ተኮር ጉዳዮች ላይ ባቀረበው ዝርዝር ሪፖርቱ በሚቀጥሉት አምስት አመታት ውስጥ የባዮሜትሪክ ቴክኖሎጂ ዘርፍ በከፍተኛ መጠን እንደሚያድግ ጠቁሟል፡፡

ተቋሙ እስከ 2020 የባንክ ተጠቃሚዎች የማንነት መለያዎችን በስልኮቻቸው በመሙላት እና በማረጋገጥ ብቻ 1.9 ቢሊዮን ተጠቃሚዎች ከኤቲኤም ይልቅ የባዮሜትሪክ የባንክ አገልግሎት ቴክኖሎጂን ይጠቀማሉ ብሏል፡፡

እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጣር እስከ 2023 ደግሞ 586 ሚሊዮን የባንክ ደንበኞች የባዮሜትሪክ ቴክኖሎጂ የባለቤትነት ማረጋገጫዎችን በስልኮቻቸው በመጠቀም በስልኩ የዲጂታል ሲስተምን በመጠቀም ገንዘቦችን ከኤቲኤሞች ማውጣት ችላሉ ተብሏል፡፡

https://www.infosecurity-magazine.com/news/cloud-biometrics-use-to-soar-next/