ናይጄሪያ የሳይበር ወንጀልን 70 በመቶ ለመቀነስ እንደምትሰራ አስታወቀች

ዘጋርዲያንን ዋቢ አድርጎ አይቲ ኒውስ እንደዘገበው ናይጄሪያ የሳይበር ወንጀል እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለመከላከል ጠንክራ እንድምትሰራ አስታውቃለች፡፡ በናይጄሪያ ከግለሰብ እስከ ታላላቅ ተቋማት ድረስ በሚደርሰው የሳይበር ወንጃል በዓመት ከ214 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ኪሳራ እንደሚያስከትል ተጠቁሟል፡፡ የአገሪቱ ብሔራዊ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ልማት ኤጀንሲ (NITDA) ጄኔራል ዳይሬክተር ኢሳ ፓንታሚ እንደገለጹት ችግሩን 70 በመቶ ለመቀነስ ስትራቴጅክ ዕቅድ ወጥቶ እንቅስቃሴ ተጀምሯል ብለዋል፡፡ ይህን ለመፈጸምም በዋናነት በሳይበር ዙሪያ ለማህበረሰቡ የግንዛቤ ፈጠራዎችን መስጠት ስኬታማ እንደሚያደርግ ታምኖበታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ወንጀሉን ለመከላከል  ፈጣን ውሳኔዎችንና እንቅስቃሴዎችን ለመፈጸም ስምምነት ላይ ተደርሷል ያሉት ዳይሬክተሩ እንደ አስፈላጊነቱም በአገሪቱ የሳይበር ወንጀልን ለመከላከል የሚያስችሉ  ሌሎች ዲፓርትመንቶችን ለማቋቋም ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡   

http://www.itnewsafrica.com/2017/08/nitda-how-nigerians-can-cut-cyber-crime-by-70