አፕል እና የሜሪካው ኤፍቢአይ (FBI)ውዝግብ ውስጥ ገቡ

አፕል እና የአሜሪካዉ የፌዴራል ምርመራ ቢሮ (FBI) ውዝግብ ውስጥ የገቡት ለአፕል ከፍርድ ቤት በመጣ ትዕዛዝ መሰረት አፕል ባለፈው ጊዜ በከሊፎርኒያ ሳን በርናርዲኖ (San Bernardino) አከባቢ የተፈፀመውን እና አሸባሪ ቡዱኑ አይ ኤስ ሀለፊነቱን የወሰደውን ጥቃት ያደረሱትን ግለ-ሰቦች ስልክ ልዉዉጦችን ለማወቅ የግለሰቦቹን ስልክ እንዲከፍት በመጠየቁና አፕልም የደንበኞቼን መረጃ በፍፁም ለማንም አካል አሳልፌ አልሰጥም በማለቱ ነዉ፡፡ 
የአፕል ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ቲም ኩክ በመግለጫቸዉ "የአይፎን ስልክ ተጠቃሚ የሆነዉን የደንበኛቸዉን የሪዝዋን ፋሩቅን ስልክ የይለፍ ቃል እንድንከፍት በኤፍቢአይ ጠያቂነት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ቢላክብንም የደንበኞቻችንን መረጃዎች አሳልፈን ለማንም ባለመስጠት በደንበኞቻችን ላይ እምነት ማሳደር እንደሚጠበቅብን እንፈልጋለን" ሲሉ ተናግረዋል፡፡ 
መንግስት አፕልን እየጠየቀን ያለው የራሳችንን ደንበኞች መረጃዎች እንድንመነትፍና የደንበኞቻችንንና በአስር (10) ሚሊየን የሚቆጠሩ የአሜሪካን ዜጎች የደህንነት ጉዳይ ችላ እንድንል ነው በማለት አፕል ለአሸባሪዎች ፍቅር ኖሮት ሳይሆን ትዕዛዙን የተቃወመው እንደዚህ አይነት እንቅስቃሴዎች የአፕልን ደንበኞች የደህንነት ስጋት ውስጥ የሚጥል ስለሆኑ ብቻ አንተባበርም ማለታቸዉን ገልፀዋል፡፡
ኤፍቢአይ የፋሩቅን ስልክ ለመክፈት የተለያዩ ሙከራዎችን አድርጎ ስላልተሳከለት እና ስልኩ ላይ ያለውን መረጃ ደጋግሞ በመሞከሩ ከነጭራሹም እንዳያጠው በመፍራቱ ነው አፕል ስልኩን በመክፈት እንዲተበበረው የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ያስወጣውም ተብሎዋል፡፡ 
ለበለጠ መረጃ የሚከተሉትን ሊንኮች ይጫኑ፡- http://www.presstv.com/…/apple-san-bernardino-iphone-us-cal… http://edition.cnn.com/…/san-bernardino-shooter-…/index.html