ጂ-ሜይል (Gmail) በቀድሞዎቹ የክሮም፣ዊንዶው ኤክስፒ እና ቪስታ ምርቶች አገልግሎቱን ሊያቆም አንደሆነ ገለጸ

ጉግል ከደህንነት ስጋት ጋር በተያያዘ የጂ-ሜይል (Gmail) አገልግሎቱን በቀድሞዎቹ የክሮም፣ዊንዶው ኤክስፒ እና ቪስታ መስጠቱን ሊያቆም አንደሆነ ነው ያስታወቀው፡፡ የክሮም(Chrome) ተጠቃሚዎችም እ.ኤ.አ. ከፌብርዋሪ 8፣ 2017 ጀምሮ የጂ-ሜይል አገልግሎት ለማግኘት የቅርብ ጊዜ ውጤችን ክሮም 54 እና 55 እንዲጠቀሙ ጉግል አሳስቧል፡፡ ከእነዚህ ውጪ ያሉ የክሮም ውጤቶች አገልግሎታቸው እንደሚቋረጥም ጠቁሟል፡፡ የዊንዶው ኤክስፒ( Windows XP) እና ዊንዶው ቪስታ ( Vista OS) ኦፕሬቲንግ ሲስተም ተጠቃሚዎች እነዚህን የዊንዶው ምርቶች እንዳይጠቀሙ የመከረ ሲሆን ይህ ባይሆን የጂ-ሜይል አገልግሎታቸውን እንደሚያቋርጥም ገልጧል፡፡ በተጠቀሱት የቆዩ ምርቶች ጂ-ሜይል የሚጠቀሙ ከሆነ ተጠቃሚዎቹ ለመረጃ ጥቃት የተጋለጡ እንደሆኑና አዳዲስ የሚወጡ የክፍተት መሙያዎችን (bugfixes) ማግኘት እንደማይችሉም አሳውቋል፡፡ በመጨረሻም የጉግል ተጠቃሚዎች ማይክሮሶፍት የተዋቸውን የዊንዶው ኤክስፒ እና ቪስታ ምርቶችን በመተው ደህንነታቸው በተሻለ ደረጃ ላይ የሚገኙትን አዳዲሶችን የማይክሮሶፍት ምርቶች መጠቀም ይገባል ብሏል፡፡

ለተጨማሪ፡- https://www.techworm.net/2017/02/windows-xp-vista-users-beware-google-stopping-gmail-os.html