Skip to Content
  • Drop an Email contact@insa.gov.et
  • Get in Touch +251-113-71-71-14

Asset Publisher Asset Publisher

Back

የኢመደኤ ሰራተኞችና አመራሮች ከቡራዩ እና አካባቢው ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን ድጋፍ አድርገዋል

 

 

አዲስ አበባ፤መስከረም 11/2011 -የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) ሰራተኞችና አመራሮች ከቡራዩ እና አካባቢው ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን የቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል፡፡ በመድሃኒዓለም ትምህርት ቤት በመገኘት አስፈላጊ ናቸው የተባሉ ለህፃናትና ሴቶች የሚሆን የአልሚ ምግብና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን አበርክተዋል፡፡ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አጀንሲ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጥ/ዳይሬክተር አቶ አብዱልባሲጥ አህመድ በቦታው ተገኝተው እንደተናገሩት የኢመደኤ ሰራተኞችና አመራሮች ከህዝብና ከመንግስት የተሰጣቸውን ተልዕኮ ከመወጣት ባሻገር በተለያዩ ጊዜያት በተፈጥሮና ሰውሰራሽ አደጋዎች ለተጠቁ ወገኖቻችን ድጋፍ ማድረጋቸውን አስታውሰው የዛሬውን ድጋፍም  ያደረጉ በተለይም ችግር ፈች ናቸው ተብለው የታመነባቸውን ቁሳቁሶች በመለየት ሲሆን ይህምህጻናት እናቶች እንዲሁም በቦታው ላይ ለተወለዱ ህፃናት  የሚሆን ነው ብለዋል፡፡ ርክክቡን ያደረጉት በጉለሌ /ከተማ የሰራተኛና ማህበራዊ /ቤት ኃላፊ አቶ አየለ መኮንን በበኩላቸው በርካታርዳታዎች ተደርገዋል፣ ሆኖም የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አጀንሲ አመራርና ሠራተኞች ያደረጉትን ድጋፍ ለየት የሚያደርገው አስፈላጊ እና አንገብጋቢ የሆኑትን ቁሳቁሶች ለይተው በማምጣታቸው እነደሆነ ተናግረው ለዚህም አመስግነዋል፡፡

 


ደህንነቱ የተጠበቀ ሳይበር ለሰላም ፣ ለልማትና ዲሞክራሲ

   ሳይበርኛ የቴሌቪዥን ፕሮግራም

ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ

ራዕይ

  • በ2017 ዓ/ም ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ብቃት ያለው እና በሀገሪቱ ህዳሴ ቁልፍ ሚና የሚጫወት ብሄራዊ የሳይበር ሴኪዩሪቲ ተቋም እውን ማድረግ፡፡   

ተልዕኮ

  • የአገሪቱን ኢንፎርሜሽን እና የኢንፎርሜሽን መሰረተ ልማትን ከጥቃት ለመከላከል የሚያስችል አቅም በመገንባት ብሔራዊ ጥቅሞችን ማስጠበቅ፡፡

እሴቶች

  • ተዓማኒነት
  • ሁሌም መማርና ማደግ
  • ልዩነት መፍጠር 
  • ተጠያቂነት

Web Content Display Web Content Display

 
 
INSA

ያግኙን ያግኙን

ስልክ: +251-11-371-71-14
ፖ.ሣ.ቁ: 124498
ኢሜል: contact@insa.gov.et
ፋክስ: +251-11-320 40 37
አድራሻ: አዲስ አበባ,ኢትዮጵያ