ዜና ዜና

በቴሌኮም ማጭበርበር አዋጅ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) በቴሌኮም ማጭበርበር አዋጅ ቁጥር 761/2004 ዙሪያ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ዳኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡ ስልጠናው ጥር 6 ቀን 2009 ዓ.ም ለግማሽ ቀን ያህል የተሰጠ ሲሆን፤ በስልጠናው ላይ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ዳኞች ፕሬዝዳንት አቶ በላቸው አንችሳ እንዲሁም የኢመደኤ ም/ዋ/ዳይሬክተር ሻለቃ ቢኒያም ተወልደ ተገኝተዋል፡፡

የኢመደኤ አመታዊ የውስጥ የስፖርት ውድድር ተጀመረ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) በየአመቱ የሚያካሂደው የውስጥ የስፖርት ውድድር ታህሳስ 27 ቀን 2009 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ ተጀመረ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር “ስፖርት ለሁሉም” ውድድር ተጀመረ

7ኛው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስፖርት ለሁሉም ውድድር ታህሳስ 22 ቀን 2009 ዓ.ም በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በድምቀት ተጀመረ፡፡

ኢመደኤ ብሔራዊ የሳይበር መከላከል ልዩ የተሰጥኦ ውድድር አዘጋጀ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) በአይነቱ ልዩ የሆነና በሳይበር መከላከል ዙሪያ ልዩ ተሰጥኦ ላላቸው ኢትዮጵያዊያን በሙሉ (ከ18 አመት በላይ፣ በማንኛውም ጾታ እና በየትኛውም የትምህርት ደረጃ ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ) የቀረበ የሳይበር መከላከል ልዩ የተሰጥኦ ውድድር ማካሄድ ጀመረ፡፡

በኢመደኤ የሳይበር መከላከል ተሰጦ ውድድር

በኢመደኤ የሳይበር መከላከል ተሰጦ ለመወዳደር ይህን በመጫን የመመዝገቢያ ፎርሙን ማግኘት ይችላሉ፡፡ ፎርሙን ከሞሉ በኋላ ደግሞ በሚከተለው አድራሻ ይላኩት ፡- cybertalentethiopia@insa.gov.et

ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ 11ኛውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በደመቀ ሁኔታ አከበረ

11ኛው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን “ህገ-መንግስታችን ለዴሞክራሲያዊ አንድነታችን ለህዳሴያችን” በሚል መሪ ቃል የኤጀንሲው አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፡፡

በደህንነት ቁጥጥር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) ወደ አገር በሚገቡና ከአገር በሚወጡ የመረጃና የመረጃ መገናኛ መሳሪያዎች የደህንነት ቁጥጥር (Security Inspection) ዙሪያ እንዲሁም በቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀል ዙሪያ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በፍተሻ ስራ ላይ ለተሰማሩ

በመንግስትና በቁልፍ የግል ተቋማት የሳይበር ደህንነት አቅም ለመፍጠር የሚያስችል ስታንዳርድ ፀደቀ

የኢንፎርሜሽንና ኮምፒዩተርን መሰረት ያደረጉ ቁልፍ መሰረተ ልማቶች ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ብሄራዊ የፖሊሲ የህግ፣ የስታንዳርድና ስትራቴጂ ረቂቆችን የማዘጋጀትና ሲፀድቁም ተፈፃሚነታቸውን መከታተል አንዱ ነው፡፡ በቅርቡ ኤጀንሲው በመንግስትና በቁልፍ የግል ተቋማት የሳይበር ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ስታንዳርድ (Critical Mass Cyber Security Requirement Standard) በስራ ላይ እንዲውል በዋና ዳይሬክተሩ አፅድቋል፡፡ ስታንዳርዱ ተቋማት የኢንፎርሜሽን ደህንነት ስጋቶችን መቆጣጠር እንዲችሉ ወሳኝ የሳይበር ደህንነት አቅሞችን እና ሂደቶችን (Capabilities and Processes) ቀጣይነቱን ሊያረጋግጥ በሚችል መልኩ እንዲገነቡ የሚያስችል ነው:: ስታንዳርዱ ከሳይበር ደህንነት አመራር፣ አገዛዝ እና አስተዳደር (leadership, governance and management) እንዲሁም ከሰው ሃይል እና ቴክኖሎጂ አንፃር መፈጠር ያለባቸውን አቅሞች የሚያስቀምጥ ሲሆን የሳይበር ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚያስፈልጉ ሂደቶችንም አጠቃልሎ ይዟል፡፡ ስታንዳርዱ በመንግስትና በቁልፍ የግል ተቋማት ተግባራዊ መደረግ ያለበት (አስገዳጅ) ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በመጀመሪያው ዙር ለተካተቱ ተቋማት እና ለሌሎች ባለ ድርሻ አካላት እየተሰራጨ ይገኛል፡፡ በቀጣይም ስታንዳርዱ ሌሌሎች ተቋማት የሚደርስ ሲሆን በስታንዳርዱ ዙሪያ ጥልቅ ግንዛቤ እና አቅም በመፍጠር ተግባራዊነቱን ለማገዝ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና አቅም ግንባታ ስራዎች እንደሚከናወኑ ተገልጧል፡፡ ስታንዳርዱን በዚህ ገፅ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ብሔራዊ የስፓሻል ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ፖሊሲ ጸደቀ

በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) የተዘጋጀው ብሔራዊ የስፓሻል ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ፖሊሲ ጥቅምት 4 ቀን 2009 ዓ.ም ጸደቀ፡፡ የሚኒስትሮች ም/ቤት ጥቅምት 4 ቀን 2009 ዓ.ም ባካሄደው 16ኛ መደበኛ ስብሰባ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) ተዘጋጅቶ በቀረበው ብሔራዊ የስፓሻል ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ከተወያየ በኋላ ማሻሻያዎችን በማከል ፖሊሲው በስራ ላይ እንዲውል ም/ቤቱ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡ የፖሊሲው ዋነኛ ዓላማ የስፓሻል ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ባለቤትነትን በማረጋገጥና በመጠቀም ጥራቱን የጠበቀ ወቅታዊና አስተማማኝ ስፓሻል ኢንፎርሜሽን ለሁሉም ተጠቃሚዎች በማቅረብ የሀገሪቱን የልማት ግቦች ለማሳካት ድጋፍ ማድረግ ሲሆን፤ ከዚህም በተጨማሪ በስፓሻል ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ አማካኝነት የሚፈጠሩ ስጋቶችን በመቀነስ የሀገር ደህንነትን ማስጠበቅ የፖሊሲው ሌላው ዓላማ ነው፡፡

በቴሌቪዥን ዲጂታላይዜሽን ሃገር አቀፍ ፕሮጀክት ትግበራ ዙሪያ ውይይት ተደረገ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢ.መ.ደ.ኤ) በቴሌቪዥን ዲጂታላይዜሽን ዙሪያ ከፌደራልና ክልሎች ከተውጣጡ የመንግስትና የግሉ የሚዲያ አካላት ጋር ለግማሽ ቀን የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡