የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ(ኢመደኤ) በቴክኖሎጂ ዘርፍ የሃገራችን ህዳሴ ዕውን የሚሆነው በመስኩ ከተሰማሩ ሃገር በቀል ተቋማት ጋር በቅንጅት አብሮ በመስራት እንደሆነ ያምናል። በመሆኑም በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂና ተዛማጅ ዘርፎች ዙሪያ የተሰማራችሁ፣ የተቀመጡትን መስፈርቶች የምታሟሉና በመስኩ ከኤጀንሲው ጋር ለመስራት ፍላጎቱ ያላችሁ ሃገር በቀል  ተቋማት  የተዘጋጀውን ቅፅ በመሙላት እንድትመዘገቡ እንጋብዛለን።

የሚያስፈልጉ ህጋዊ ማስረጃዎች

 • በዘርፉ የተሰማሩ ሆነው የዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው
 • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ያላቸው  
 • የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው  
 • የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው
 • የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሠጠ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

የድርጅቱ ፕሮፋይል

 • ካፒታል(የገንዘብ አቅም)
 • የሰው ሀይል አቅም አና ብዛት
 • ተዛማችነት ባላቸው ዘርፎች  ላይ እውቅና ያለው ሰርተፍኬቶች  
 • በተጨባጭነት ስራ ላይ የዋሉ ፕሮጀክቶች
 • ድርጅቱ ስለ የሚጠቀምበት ቴክኖሎጂ ፥ፍሬምወርክ(Framework) 
 • ድርጅቱ ያለው መሰረታዊ የቴክኖሎጂ ግባቶች(Technology Infrastracture)

ከላይ የተጠቀሱ ማስረጃዎችን እና ይጠቅማሉ የምትሉትን ማንኛውንም መረጃ  አንድ ላይ በድርጅቱ ስም ዚፕ በማድረግ ይላኩ:: አጠቃላይ የመረጃው መጠን ከ20MB መብለጥ የለበትም:::: እንዲሁም በሚከተሉት ፎርማት መላክ ይቻላል .doc,.docx,.pdf

ለመመዝገብ እዚህ ጋር ይጫኑ