የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና የሚዲያ ጉዳዮች ሃላፊ ታላል አል አዘሪ ጋር ተወያዩ

التطبيقات المتداخلة

ناشر الأصول

ሥነ-ምግባራዊ አመራር ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት በሚል ርዕስ ለኢመደአ፣ ለኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ እና ለፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት አመራሮች ስልጠና እየተሰጠ ነው ፡፡

ሥነ-ምግባራዊ አመራር ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት በሚል ርዕስ ለኢመደአ፣ ለኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ እና ለፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት አመራሮች ስልጠና እየተሰጠ ነው ፡፡ الأربعاء, ٥ Feb ٢٠٢٥

በብሄራዊ የሳይበር ደህንነት ማዕቀፎች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የአተገባበር ሂደት ላይ ስልጠና ተሰጠ

በብሄራዊ የሳይበር ደህንነት ማዕቀፎች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የአተገባበር ሂደት ላይ ስልጠና ተሰጠ الأربعاء, ٥ Feb ٢٠٢٥

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን የሥራ ውል ስምምነት ተፈራረሙ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን የሥራ ውል ስምምነት ተፈራረሙ الأربعاء, ٥ Feb ٢٠٢٥

የሳይበር ደህንነት አገልግሎቶች

የሳይበር ደህንነት አገልግሎቶች الجمعة, ٣١ Jan ٢٠٢٥

ناشر الأصول

null የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና የሚዲያ ጉዳዮች ሃላፊ ታላል አል አዘሪ ጋር ተወያዩ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና የሚዲያ ጉዳዮች ሃላፊ ከሆኑት ታላል አል አዘሪ ጋር በሳይበር ደህንነት እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሄዱ፡፡

በዉይይቱም የሳይበር ቴክኖሎጂ ባለቤትነትን በማረጋገጥና በዘርፉ ያለዉን የሰዉ ሃይል እጥረት በመቅረፍ ረገድ በጋራና በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

ኢመደአ የኢትዮጵያን የሳይበር የቴክኖሎጂ ባለቤትነትን ለማረጋገጥ እየሰራ ያለዉ ስራ ለሌሎች አፍሪካ አገራት ምሳሌ ሊሆን የሚችል መሆናቸዉን የጠቀሱት ታላል አል አዘሪ ይህ መልካም ተሞክሮ ወደ ሌሎች አፍሪካ አገራት መስፋት የሚገባዉ መሆኑን ገልጸዋል። አያይዘውም በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ኤምባሲ ከኢመደአ ጋር በሳይበር ደህንነት ዘርፍ በይበልጥ በታዳጊዎች የሳይበር ታለንት ልማት ላይ በትብብር መስራት ፍላጎት እንዳለዉ ሚስተር ታላል ገልጸዋል።

የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ በበኩላቸው ኢመደአ በሳይበር ቴክኖሎጂ ባለቤትነት እንዲሁም በሳይበር ታለንት ልማት ያካበተውን ተሞክሮ ለሌሎች የአፍሪካ ሐገራት ለማካፈል ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ ሰለሞን ሶካ ከታላል አል አዘሪ ጋር ካደረጉት ውውይት ባሻገር ኢመደአ ሐገራዊ የቴክኖሎጂ እና የእውቀት ባለቤትነትን በማረጋገጥ ረገድ እየሰራቸው የሚገኙ ሥራዎችን፤ የኢትዮ ሳይበር ታለንት ልማት ማዕከልን፤ እና ሌሎች ተቋማዊ ምርትና አገልግሎቶችን አስጎብኝተዋቸዋል፡፡