አስተዳደሩ ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ የስራ አመራር አባላት በሳይበር ደህንነት ዙሪያ ስልጠና ሰጠ

التطبيقات المتداخلة

ناشر الأصول

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና ሲንቄ ባንክ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና ሲንቄ ባንክ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ الثلاثاء, ٣٠ Apr ٢٠٢٤

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ሀገርን ከተለዋዋጭ የሳይበር ጥቃት መመከት የሚያስችል አቅም ገንብቷል-የፌደራል ተቋማት ሱፐርቪዥን ቡድን

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ሀገርን ከተለዋዋጭ የሳይበር ጥቃት መመከት የሚያስችል አቅም ገንብቷል-የፌደራል ተቋማት ሱፐርቪዥን ቡድን الجمعة, ٢٦ Apr ٢٠٢٤

የቴክኖሎጂ እድገትን ተከትሎ እየጨመረ የመጣዉን የሳይበር ጥቃት ለመከላከል የብሪክስ (BRICS) አባል ሃገራት በትብብርና በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ ተጠቆመ።

የቴክኖሎጂ እድገትን ተከትሎ እየጨመረ የመጣዉን የሳይበር ጥቃት ለመከላከል የብሪክስ (BRICS) አባል ሃገራት በትብብርና በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ ተጠቆመ። الخميس, ١٨ Apr ٢٠٢٤

ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ አቅም ወደፊት የሚያሻግር ነው!

ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ አቅም ወደፊት የሚያሻግር ነው! الأربعاء, ١٧ Apr ٢٠٢٤

ناشر الأصول

null አስተዳደሩ ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ የስራ አመራር አባላት በሳይበር ደህንነት ዙሪያ ስልጠና ሰጠ

 

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 16 ፣ 2014 የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ የስራ አመራር አባላት በሳይበር ደህንነት ዙሪያ የግማሽ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡

በስልጠናው መርሀ ግበር ላይ የተገኙት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሳይበር ደህንነት ጉዳይ ትኩረት ባለመሰጠቱ በርካታ ጉዳቶች እየደረሱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የሳይበር ደህንነትን ለማረጋገጥ ሶስት መሰረታዊ ነገሮችን ማሟላት ይጠይቃል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ፤እነዚህም እውቀትና ክህሎት ያለው የሰው ሃይል፣የዘመኑ ቴክኖሎጂዎችና ትክክለኛ የአሰራር ስርዓት መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ይህ ሲሟላም የሳይበር ደህንነት አስተማማኝ ደረጃ ደርሷል ማለት እንደሚቻል ዶ/ር ሹመቴ ገልፀዋል፡፡

በቀጣይም አስተዳደሩ ተመሳሳይ ስልጠና ለባንኩ አመራሮችና ሰራተኞች ለመስጠት ፈቃደኛ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚደንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው በበኩላቸው የኢንፎርሜሽን ዲጂታል ስርዓት የሀገራት መወዳደሪያ ጡንቻ በሆነበት በዚህ ወሳኝ ወቅት የተቋማት መረጃን ከማንኛውም አይነት የሳይበር ጥቃት መጠበቅ ትኩረት የሚሻ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሀገራት ሉአላዊነታቸውንና አጠቃላይ ህልውናቸውን አረጋግጠው ለመኖር የዲጂታል ቴክኖሎጂ አቅምን መገንባት አማራጭ ሳይሆን ግዴታ የሆነበት ዘመን ላይ እንገኛለን ያሉት የባንኩ ፕሬዝደንት፤ከዚህ አንጻር የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ስልጠናውን ለመስጠት ላሳየው ተነሳሽነት ምስጋናቸውንም አቅርበዋል፡፡