ID4Africa2025 ጉባኤ መካሄድ ጀመረ

ناشر الأصول

null ID4Africa2025 ጉባኤ መካሄድ ጀመረ

ዛሬ ጠዋት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በኩል በይፋ የተከፈተውን #ID4Africa2025 በማስተናገዷ፣ #ኢትዮጵያ ኩራት ይሰማታል። ID4Africa ማኅበረ ኢኮኖሚያዊ ልማትን፣ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን እና ሰብአዊ ጥረቶችን የሚያበረታቱ ጠንካራ እና ኃላፊነት የሚሰማቸው የማንነት ዐውዶችን በመገንባት፣ የአፍሪካ ሀገራትን ለመደገፍ ቁርጠኛ የሆነ የፓን አፍሪካ እንቅስቃሴ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመክፈቻ ንግግራቸው ኢትዮጵያ ከተበታተነው የመታወቂያ ሥርዓት አልፋ፣ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ወደተጀመረው አስተማማኝ፣ ሁሉንም ያካተተ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ መሸጋገሯን አጽንዖት ሰጥተዋል። ለፋይዳ እስካሁን ከ15 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተመዝግበዋል። 90 ሚሊዮን ሰዎችን ለመመዝገብ ታቅዶ እየተሠራ ነው፡፡ ፋይዳ ሁሉም ዜጎች - በተለይ ሴቶች፣ ወጣቶች እና የተፈናቀሉ ማኅበረሰቦች አስፈላጊ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ እንደሚያደርግ አሳውቀዋል።

እንደ ፋይናንስ፣ ጤና እና ትምህርት ባሉ ቁልፍ ዘርፎች የተቀናጀው ፋይዳ፣ 9.6 ትሪሊዮን ብር በዲጂታል ግብይት እንዲዘዋወር እያገዘ መሆኑንም ገልጸዋል።

التطبيقات المتداخلة

ناشر الأصول

የመጀመሪያ አለምአቀፍ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ በሀገራችን ETEX 2025.

የመጀመሪያ አለምአቀፍ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ በሀገራችን ETEX 2025. الأربعاء, ٢١ May ٢٠٢٥

የምስራቅ አፍሪካ ትልቁ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ ETEX 2025

የምስራቅ አፍሪካ ትልቁ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ ETEX 2025 الأربعاء, ٢١ May ٢٠٢٥

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የታደሙት የድሮን ትርዒት ETV | EBC | EBCDOTSTREAM

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የታደሙት የድሮን ትርዒት ETV | EBC | EBCDOTSTREAM الأربعاء, ٢١ May ٢٠٢٥

አካታች የሆነ የዲጅታል ሽግግር ለማድረግ የዲጂታል መታወቂያ ሚና ከፍ ያለ መሆኑን የኢመደአ ዋና ዳይሬክተርና የID4Africa አምባሳደር ገለፁ

አካታች የሆነ የዲጅታል ሽግግር ለማድረግ የዲጂታል መታወቂያ ሚና ከፍ ያለ መሆኑን የኢመደአ ዋና ዳይሬክተርና የID4Africa አምባሳደር ገለፁ الأربعاء, ٢١ May ٢٠٢٥