ኢትዮጵያ የሳይበር ደህንነቷን ለመጠበቅ የሚያስችል አቅም እየገነባች ትገኛለች

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ኢትዮጵያ የሳይበር ደህንነቷንና ዲጂታል ሉዓላዊነቷን ለመጠበቅ የሚያስችል አየበገሬ (Resilient) የሳይበር አቅም እየገነባች እንደምትገኝ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ገለጹ።

በተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ዱባይ እየተካሄደ ባለው የጂ.አይ.ቴክስ 2024 ኤክስፖ (GITEX2024) በተደረገ የሳይበር ደህንነት ፓናል ውይይት ላይ በፓናሊስትነት የተሳተፉት ዋና ዳይሬክተሯ የኢትዮጵያን የሳይበር ደህንነት አቅም ግንባታ ተሞክሮዎች አጋርተዋል።

ኢትዮጵያ የዲጂታል ሽግግርን ጨምሮ በሁሉን አቀፍ ፈጣን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ላይ መሆኗን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሯ በዚህ ሂደት ሊቃጡ የሚችሉ የሳይበር ደህንነት ስጋቶችን አስቀድሞ ለመከላከልም ይሁን ከተከሰቱ በኋላ በፍጥነት ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ሁሉን አቀፍ አቅም እየገነባች እንደሆነ ገልጸዋል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳድር የቅድመ ሳይበር ጥቃት መከላከል ላይ በማተኮር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል። በዚህም በተለያዩ ጊዜያት የተቃጡ የሳይበር ጥቃቶችን ማክሸፍ መቻሉን ነው የገለፁት።

ሀገራዊ የሳይበር ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚያስሉ የሕግ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት፣ በዘርፉ ብቁ የሰው ኃይል በማፍራት፣ የቴክኖሎጂ ባለቤትነትን በማረጋገጥ፣ ትብብርና ቅንጅቶችን በማጠናከር ወ.ዘ.ተ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ዋና ዳይሬክተሯ አብራርተዋል።

ለአብነትም በኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መካከል የተደረገው የ5 ሚሊዮን ኮደሮች ስምምነት በዘርፉ እየተሰራ የሚገኘውን የትብብርና ቅንጅት ስራ እንደሚያሳይ ዋና ዳይሬክተሯ ጠቁመዋል።

ሀገራዊ የሳይበር ንቃተ ሕሊና በመገንባት በኩል በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሯ፤ በየዓመቱ ወርኃ ጥቅምትን ሀገራዊ የሳይበር ወር በሚል ግንዛቤ በሚያስጨብጡ የተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር ጠቅሰዋል።

የሳይበር ደህንነት በስርዓት ትምህርት የማካተት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በሌላ በኩል በዘርፉ የሁለተኛና ሶስኛ ዲግሪ ተማሪዎችን ለማፍራትም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር የተደረገውን ስምምነት ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያ የሳይበር ደህንነትና ሰው ሰራሽ አስተውሎትን ጉዳዮችን ቁልፉ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች ስለመሆኑ አረጋግጠዋል።

የሳይበር ደህንነት ፖሊሲም የሰው ኃይል ግንባታን ከግምት ውስጥ ያስገባ ስለመሆኑ ገልፀዋል።

የሳይበር ደህንት ጉዳይ የመላው ዓለም ስጋት በመሆኑ ይህንን ለመከላከል ሀገራት በትብብርና በቅንጅት መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

ناشر الأصول


የቅርብ ዜናዎች