ኢመደአ የደመና ማበልጸጊያ ሲስተም አምርቶ ጥቅም ላይ አዋለ
Publicador de continguts
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) የደመና ማበልጸግ (CLOUD SEEDING) ቴክኖሎጂ ለሀገራችን ሊሰጥ የሚችለውን ጥቅም ታሳቢ በማድረግ በራስ አቅም ቴክኖሎጂዉን አልምቶ ወደ ስራ አስገባ።
ከዚህ ቀደም ከዉጭ ሀገራት በተለያየ መልኩ ሲገባ የነበረውን የደመና ማበልጸጊያ (ማዝነቢያ) ግራውንድ ጀነሬተር በኢመደአ በተፈጠረ ሙሉ አቅም መሥራት ተችሏል። ይህም የቴክኖሎጂው ባለቤትነታችንን ከማረጋገጥ ባሻገር የውጭ ምንዛሪን በማዳን ከፍተኛ ሀገራዊ ጥቅም ያለው ነው።
በራስ አቅም ቴክኖሎጂን በማበልጸግ ሂደት ዉስጥ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ይህን ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ ውሎ በሀገራችን በዝናብ እጥረት የሚያጋጥምን አደጋ ለመከላከል ከኢመደአ ጋር በትብብር እየሰራ ይገኛል።
45 የግራዉንድ ጀነሬተሮች ተመርተዉ ወደ ስራ የገቡ ሲሆን ምርቶቹ የዝናብ እጥረት በተደጋጋሚ በሚያጋጥማቸዉ የምሥራቅና ደቡብ ምሥራቅ የሀገራችን ክፍሎች ተተክለው የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት በሚሰጠው የአየር ጠባይ ትንበያ መሰረት የኦፕሬሽን ሥራ እየተካሄደ ነዉ።