ኢመደአና የኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸዉን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።
Aplicacions anidades
Publicador de continguts
Publicador de continguts
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር(ኢመደአ) እና የኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በትብብር መስራት በሚችሉባቸዉ ጉዳዮች ዙሪያ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።
በመግባቢያ ስምምነቱ ላይ የተገኙት የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ የኢፌደሪ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የሀገር ሃብት የሆኑ አትሌቶችን ጨምሮ ብርቅዬ ኢትዮጵያዊያንን መረጃ የሚይዝ በመሆኑ እነዚህን መረጃዎች ዲጂታላይዝድ የማድረግና ደህንነታቸዉን ማስጠበቅ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።
በዚህም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሚሰራቸዉ የዲጂታይዜሽን ስራዎች ኢመደአ አስፈላጊዉን ደጋፍ እንደሚያደርግ ዋና ዳይሬክተሯ ገልጸዋል።
የኢፌደሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ በበኩላቸዉ ባህልና ስፖርት ስራዎችን ማልማት ለሀገር ግንባታ የሚሰጠዉ አብርክቶ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዉ ይህን የሚመጥን ዘመናዊ የመረጃ አያያዝና ላይ ክፍተቶች መኖራቸዉን አንስተዋል።
በዛሬዉ ዕለት ከኢመደአ ጋር የተደረገዉ የመግባቢያ ስምምነትም ተቋሙን ዲጂታላይዝ በማድረግ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎቶችን በመስጠት ተቋማዊ ተልዕኮዉን ለመወጣት አጋዥ መሆኑን ጠቁመዋል።